ኬንያ ራይላ ኦዲንጋ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር እንዲሆኑ በይፋ ጠየቀች
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽኑን መምራት የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች እንዲመዘገቡ ያስቀመጠው ጊዜ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ ቀርተውታል
ከኬንያ በተጨማሪ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ሺሸልስ ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል
ኬንያ ራይላ ኦዲንጋ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር እንዲሆኑ በይፋ ጠየቀች፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ምርጫ በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት የህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃማት ስልጣን ሊጠናቀቅ አንድ ዓመት ብቻ ቀርቶታል፡፡
ይህን ተከትሎም ህብረቱ ማስታወቂያ ያወጣ ሲሆን የኬንያ ፕሬዝዳንት ለመሆን አራት ጊዜ ተወዳድረው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በይፋ ጥያቄ አቀርበዋል፡፡
የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የራይላ ኦዲንጋ ጥያቄን በአዲስ አበባ በይፋ ለአፍሪካ ህብረት አቅርቧል፡፡
የአፍሪካ ህብረት እጩ ተወዳዳሪዎች እንዲመዘገቡ ያስቀመጠው ጊዜ የፊታችን ማክሰኞ የሚያበቃ ሲሆን ኬንያ ራይላ ኦዲንጋን ዋነኛ እጩ አድርጋ አስመዘግባለች፡፡
ከኬንያ በተጨማሪ ጅቡቲ፣ ሲሸልስ እና ሶማሊያም እጩ ያስመዘገቡ ሲሆን ራይላ ኦዲንጋ የተሻለ ድምጽ ሊያገኙ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡
ከአፍሪካ ጫፍ እስከ ጫፍ የሮጠው ብሪታንያዊ በኢትዮጵያ ምን ገጠመው?
እጩዎች ከተመዘገቡ በኋላ ኢትዮጵያዊቷ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጅት ስነጊዮርጊስ አባል የሆኑት የአፍሪካ ህብረት የባለሙያዎች ቡድን እጩዎችን ገምግሞ ለመጨረሻ ዙረር ምርጫ ድምጽ እንዲሰጥባቸው ይመራል፡፡
በባለሙያዎች ውሳኔ መሰረትም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች በሚስጥር በሚዘጋጅ ምርጫ ድምጽ የሚሰጡ ይሆናል፡፡
የፊታችን የካቲት በሚካሄደው በዚህ ምርጫ ላይ እጩዎች ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት የምርጫ ቅስቀሳ የሚያደርጉ ሲሆን ከአፍሪካዊያን ጋር የጥያቄ እና መልስ እንደሚያደርጉም ይጠበቃል፡፡