የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒን በቢላዋ ሊገድል ሲሞክር የተያዘው ወታደር ሞቶ ተገኘ
ግለሰቡ የ24 ዓመት ወጣት እና የሀገሪቱ ጦር አባል ነበር ተብሏል
ፕሬዝዳንት አሱማኒ በወታደሩ በደረሰባቸው አነስተኛ ጥቃት ቆስለው እንደነበር ተገልጿል
የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒን በቢላዋ ሊገድል ሲሞክር የተያዘው ወታደር ሞቶ ተገኘ፡፡
ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኮሞሮስ ፕሬዝዳንት የሆኑት አዛሊ አሱማኒ በሀገሪቱ የሚገኝ የሀይማኖት አባት ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ስርዓተ ቀብር ላይ በተገኙበት ወቅት የግድያ ሙከራ ተፈጽሞባቸዋል፡፡
የግድያ ሙከራውን የፈጸመው የ24 ዓመት ወጣት ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት የሀገሪቱን ጦር እንደተቀላቀለ ተገልጿል፡፡
ይህ ወታደር በቢላዋ ፕሬዝዳንቱን ወግቶ ለመግደል ሲሞክር የጸጥታ ጠባቂዎች እርምጃ አቁስለውት ነበር የተባለ ሲሆን የፕሬዝዳንቱ ደህንነት ከተረጋገጠ በኋላ ወደ በሀገሪቱ መዲና ሞሮኒ ከተማ ባለ አንድ እስር ቤት ውስጥ ታስሮ ነበርም ተብሏል፡፡
ይሁንና ይህ ፕሬዝዳንቱን ያቆሰለው ወታደር በታሰረበት ክፍል ውስጥ እያለ ህይወቱ እንዳለፈ ለሞንዴ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ፕሬዝዳንቱ በቢላዋ ከተቃጣባቸው ጥቃት በኋላ የስርዓተ ቀብሩን አቋርጠው ወደ ቤተ መንግስት ተመልሰዋልም ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በበኩሉ በፕሬዝዳንቱ ላይ የግድያ ሙከራ የፈጸመው ተጠርጣሪ ህይወቱ ለምን እና እንዴት እንዳለፈ ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አሜሪካን 50 ቢሊየን ዶላር ያሳጡት አፍሪካውያን ዲጂታል አጭበርባሪዎች
የ65 ዓመቱ ፕሬዝዳንት አሱማኒ እስከ 2029 ድረስ የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ የተካሄደውን ምርጫ አሸንፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ የ40 ዓመት ልጃቸው ስልጣን እንዲይዝ ያደረጉ ሲሆን ቀስ በቀስም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ መንገድ ለመጥረግ ያለመ ህግ አጽድቀዋል የሚል ትችቶች ቀርቦባቸዋል።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ የፕሬዝዳንቱ ወንድ ልጅ ኤል ፋዝ አዲስ ስልጣን የተሰጣቸው ሲሆን የሀገሪቱን ሁሉንም ተቋማት እና አመራሮች እንዲገመግሙ ይፈቅድላቸዋል።