የአሜሪካው ወልማርት 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ሰራተኞችን በመቅጠር ቀዳሚው ነው
በ2023 የተቀጣሪ ሰራተኞች ቁጥር 3 ነጥብ 5 ቢሊየን መድረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።
ይህም በፈረንጆቹ 1991 ከነበረበት 2 ነጥብ 23 ቢሊየን ከ1 ቢሊየን በላይ ጭማሪ ያሳየ ነው።
ከተቀጣሪ ሰራተኞቹ ውስጥ 2 ነጥብ 1 ቢሊየኑ ወንዶች መሆናቸውን የሚጠቅሰው ስታስቲካ፥ በርካታ ሰራተኞችን በመቅጠር የአሜሪካው የችርቻሮ ንግድ ኩባንያ ወልማርት ቀዳሚው መሆኑን ይጠቅሳል።
በ2023 640 ቢሊየን ዶላር ገቢ ያስገባው ወልማርት፥ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ቀጥሮ ያሰራል።
ሌላኛው የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አማዞን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰራተኞችን በመቅጠር ይከተላል።
የተቋማትን የሰራተኞች ቁጥር፣ ገቢ እና ተያያዥ መረጃዎች የሚያጋራው “ካምፓኒስኔትካፕ” ድረገጽ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት 10 ኩባንያዎች እያንዳንዳቸው ከ500 ሺህ በላይ ሰራተኞች ቀጥረው ያሰራሉ።
በርካታ ሰራተኞች ቀጥረው የሚያሰሩትን ኩባንያዎች ይመልከቱ፦