ጀርመን በሰራተኛ እጥረት ምክንያት ሳምንታዊ የስራ ቀኗን ወደ አራት ቀናት ዝቅ አደረገች
አዲሱ የስራ ሳምንት ለስድስት ወራት ለሚከራ እንደሚቆይ ተገልጿል
ጀርመን በሰራተኛ እጥረት ምክንያት በዓመት 90 ቢሊዮን ዩሮ እያጣች ነው ተብሏል
ጀርመን በሰራተኛ እጥረት ምክንያት ሳምንታዊ የስራ ቀኗን ወደ አራት ቀናት ዝቅ አደረገች፡፡
የአውሮፓ ግዙፍ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ጀርመን ሳምንታዊ የስራ ቀኗ ላይ ማሻሻያ አድርጋለች፡፡
ሀገሪቱ በሳምንታዊ የስራ ፕሮግራሟ ላይ ማሻሻያ ያደረገችው የሰራተኛ እጥረት በማጋጠሙ እንደሆነ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ጀርመን የሰራተኞች እጥረት የገጠማት ሲሆን በስራ ላይ ያሉት ሰራተኞችም ደስተኛ እና ምርታማ ሆነው እንዲሰሩ በሚል በ45 ተቋማት ላይ ለሙከራ የስራ ቀናቸውን በሳምንት ወደ አራት ቀናት ዝቅ እንዲል ወስናለች፡፡
ለስድስት ወራት ይቆያል የተባለው ይህ አዲሱ የስራ ቀናት በተመረጡ ተቋማት ውጤታማ ከሆነ በቀጣይ ትግበራው ሀገር አቀፍ ሊሆን እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
ስራው አራት ቀናት ይሁን እንጂ ክፍያው የሙሉ ሳምት ነው የተባለ ሲሆን አዲሱ የስራ ስርዓት በርሊን ያለ አንድ የጥናት ተቋም ያቀረበውን ጥናት መሰረት በማድረግ ነውም ተብሏል፡፡
ጀርመን በሀገሯ ከሶስት ዓመት በላይ ለኖሩ ዜጎች ዜግነት ልትሰጥ ነው
በጀርመን ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የሰራተኞች ምርታማነት እየቀነሰ ቢመጣም ከሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ግን የተሻለ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አዲሱን የስራ ቀናት መተግበር የጀመሩ ሰራተኞች እንዳሉት በሳምንት አራት ቀናት መስራት የበለጠ የስራ ላይ ደስታ እና ምርታማ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል፡፡
አዲሱ ለሙከራ እየተተገበረ ያለው ይህ የሰራ ቀናት በጫና ምክንያት ከስራ ውጪ የነበሩ ጀርመናዊያንን ወደ ስራ ሊመልሳቸው ይችላልም ተብሏል፡፡
ጀርመን የሰለጠኑ ባለሙያዎች እጥረት ያለባት ዋነኛዋ የአውሮፓ ሀገር ስትሆን በዚህ እጥረት ምክንያት በዓመት 90 ቢሊዮን ዩሮ እያጣች እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡