ባለ ሁለት መቀመጫዋ መኪና በፈረንጆቹ 2024 ለገበያ ትቀርባለች ተብሏል
የህንድ የመኪና አምራች ቫይቭ ሞቢሊቲ በሀገሪቱ የመጀመሪያኃ በጸሀይ ኃይል የምትሰራ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ይፋ አደረገ።
ባለ ሁለት መቀመጫዋ በፀሃይ ኃይል የምትሰራው መኪናዋ ኃይል ለመሙላት የሚያስችላት የሶላር ፓኔሎች በጣሪያ ላይ የተገጠሙላት ነው።
ስማርት መኪናዋ “ኢቫ” የሚል ስያሜ የተሰጣት ሲሆን በባትሪ ማሸጊያው ላይ በቀን እስከ 10 ኪሎ ሜትር (6.2 ማይል) እንድትሄድ የሚያስችል ተጨማሪ ቻርጅ ለማድረግ በጣሪያዋ ላይ የሶላር ፓነሎች ያላት ናት።
የቫይቭ ሞቢሊቲ ዋና ስራ አስፈጸሚ መኮንን ቪላስ ተሽከርካሪውን በ18 ወራት ውስጥ ማትም በፈረንጆቹ 2024 አጋማሽ ወደ ገበያ ለማቅረብ እቅድ መያዙን ተናግረዋል።
የአካባቢ ኃይልን የማይበክለው የበጸሀይ ኃይል መኪና የህንድ መንግስት የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ አስቦ በመስራት ላይ ባለበት ወቅት ነው ይፋ የተደረገችው።
ህንድ የመኪና አምራች ኩባንያዎቿ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን እንዲያመርቱ ለማስቻል በሚሊየን የሚቆጠሩ ዶላሮችን አቅርባላቸዋለች።