የሞባይል ስልኩ ግድብ ውስጥ የገባበት ባለስልጣን 2 ሚሊየን ሊትር ግድብ ውሃ እንዲለቀቀ አደረገ
ባለስልጣኑ ስልጣንን አለአግባብ በመጠቀም በሚል ከስራ ታግዷል
ለባለስልጣኑ ስልክ ሲባል ከግድብ የፈሰሰው ውሃ ከ6 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መስኖ የማልማት አቅም ነበረው
የሞባይል ስልኩ ከእጁ አምልጦት ግድብ ውስጥ የገባበት ህንዳዊ ባለስልጣን ለስልኩ ሲል የግድቡን ዉሃ አስመጠጠ።
ህንድ አንድ ባለስልጣን ሰልፊ ፎቶ ራሱን ለማንሳት ሲሞክር ስልኩ ወደ ግድቡ ውስጥ ይገባበታል።
ይህ የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን 1 ሺህ 200 ዶላር ዋጋ ያለቀው ሳምሰንግ የእጅ ስልኩ ወደ ግድቡ ገብቶብኛል፣ ስልኩ በርካታ እጅግ አንገብጋቢ የመንግስት መረጃዎችን ይዟል በሚል ግድቡ እንዲመጠጥ አስደርጓል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ባለስልጣኑ መጀመሪያ ላይ ስልኩን ለማስወጣት በአካባቢው ያሉ ዋናተኞችን ቢያሰማራም አለመገኘቱን ተከትሎ በውሃ መሳቢያ ፓምፕ የግድቡ ውሃ እንዲመጠጥ አስደርጓል ተብሏል።
ራጂሽ ቪሽዋስ የተባለው ይህ ባለስልጣን ስልኩን ለማግኘት ሲባል ባለሙያዎች የግድቡን ውሃ ለመምጠጥ እና ለማፍሰስ ሶስት ቀናት እንደፈጀባቸው ተገልጿል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ ስልክ ቢገኝም በውሃ ተሞልቶ የመስራቱ ነገር አጠራጣሪ ነው የተባለ ሲሆን ጉዳዩ በህንድ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
ይህን ተከትሎም የሐገሪቱ መንግስት ባለስልጣኑ በፈጸመው ድርጊት ስልጣኑን ያለ አግባበብ በመጠቀም ከስራ የታገደ ሲሆን ጉዳዩ አሁንም መነጋገሪያነቱን ቀጥሏል ተብሏል።
ለዚህ ባለስልጣን ሲባል እንዲመጠጥ እና እንዲባክን የተደረገው ውሃ ከስድስት ሺህ በላይ ሄክታር መሬት መስኖ የማልማት አቅም እንደነበረው ተገልጿል።