የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊት ምን ፋይዳ አለው?
ኩባንያዎች የተለመደ ስራቸውን እየሰሩ የማህበረሰቡን እና አካባቢያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ይንቀሳቀሳሉ
የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት የንግድ ኩባንያዎች ትርፍ ከመሰብሰባ ያለፈ ኃላፊነት እንዳለባቸው የሚገልጽ ጽንሰ ሀሳብ ነው
የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት ወይም 'ኮርፖሬት ሶሺያል ሪስፖንሲቢሊቲ' ማለት የንግድ ኩባንያዎች ትርፍ ከመሰብሰባ ያለፈ ኃላፊነት እንዳለባቸው የሚገልጽ ጽንሰ ሀሳብ ነው።
ኩባንያዎች የተለመደ ስራቸውን እየሰሩ የማህበረሰቡን እና አካባቢያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ይንቀሳቀሳሉ።
አንድ ኩባንያ ትርፍ ለማግኘት እንደሚያቅደው ሁሉ የማህበረሰባዊ እና አካባቢያዊ ችግሮችን በመፍታት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ይወጣል፤ በማህበረሰቡ እና በአካባቢ ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ያሳድራል።
የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊን ሶስት ምሰሶዎች
1. ማህበራዊ ተጽዕኖ፦
ኩባንያዎች ለማህበረሰቡ በበርካታ መንገዶች አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ትምህርት፣ በጎ አድራጎት እና ጤና ኩባንያዎች ማህበረሰቡን ለመደገፉ የሚሳተፉባቸው ዘርፎች ናቸው።
2 የአካባቢ ዘለቄታዊነት
ኩባንያዎች በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ሊኖር የሚችልን ከባቢያዊ ጉዳት ለመቀነስ ይንቀሳቀሳሉ። ኩባንያዎች ታዳሽ ኃይልን በመጠቀም እና ከአካባቢ ሰነ ምህዳር ጋር የሚጣጣም የአመራረት ዘዴዎችን በመተግበረ ብክለት እንዲቀንስ ይሰራሉ።
3 ኢቲካል ቢዝነስ ፕራክቲስ
ስነምግባርን የተላበስ የቢዝነስ ስራ ለማህበራዊ ኃላፊነት ወሳኝ ነው። ይህም ግልጸኝነት ማስፈንን፣ ሰብአዊ መብት ማክበርን እና የብዝበዛ አሰራርን ማስወገድን ይይዛል።
ኩባንያዎች ባህበራዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለራሳቸው የሚያስገኝላቸው ጥቅምም አለ።
ለማህበራዊ ኃላፊነት ቁርጠኛነት ሲኖር የኩባንያው ስም እና ብራንድ በደንበኞች ዘንድ ታዋቂነትን ያገኛሉ።
የሰራተኞችን ሞራል በማሳደግ ሰራተኞች ለኩባንያው የበለጠ ቁርጠኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።
ይሁን እንጂ ማህበራዊ ኃላፊነት ምንም ፈተና የለውም ማለት አይቻልም። ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ የአጭር ጋዜ የፋይናንስ ጫና ያስከትልባቸዋል።
በአጠቃላይ ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ዘላቂ እድገት እንዲሁም በኩባንያዎች እና በማህበረሰቡ መካከል ጤናማ ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል።