አጠቃላይ ባህሪያቸውን መረዳት፣ በየጊዜው ማሻሻልና መቀየር ያለባቸውን ስርዓቶች መቀየር ይገባል፡፡
የኮምፒውተሮቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
በግለሰብ ሆነ በተቋማት ደረጃ የምንጠቀማቸው ኮምፒውተሮች ሁልጊዜ ለተለያዩ አይነት ውስጣዊና ውጫዊ ጥቃቶች የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡
የኮምፒውተሮችን አጠቃላይ ባህሪ መረዳት፣ በየጊዜው ማሻሻልና መቀየር ያለባቸውን ስርዓቶች በማወቅ መረጃዎቻችን ባልጠበቅነው መንገድ ጠፍተው ጉዳት እንዳይደርስብን አስቀድመን ጥንቃቄዎችን ልንወስድ ይገባል፡፡
ልንወስዳቸው ከሚገቡ ጥንቃቄዎች መካከል
ጠቃሚ ፋይሎችን መጠባበቂያ (backup) መያዝ
የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ሥርዓት ለደህንነት ሥጋት እንዳይጋለጡ የኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን ክፍተት መሙላት/ Apply patches to the operating system/
ጸረ-ቫይረስ/Anti Virus/ሶፍትዌሮችን መጠቀም፣ በየጊዜው መተግበሪያዎችን ማዘመን (updates) እና ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ አጠቃላይ የኮምፒውተር ስርዓት ስካን (Scan) ማድረግ፤
አጥፊ ሶፍትዌሮችን የሚከላከሉ ፀረ-አጥፊ ሶፍትዌሮችን መጠቀም እና ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ስካን ማድረግ፤
የተመጠነ የፋይል አስተዳደር መተግበር እና ዲስኮቻችንን በየጊዜው ማፅዳት/disk cleanup/ የሚሉት ይገኙበታል፡፡