በኤሮስፔስና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዙርያ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን በሰፊው ለማሳተፍ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ፡፡
በኤሮስፔስና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዙርያ ከኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጋር ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በዘርፉ ከተሰማራው ሃገር በቀሉ ፊንፊኔ ኤሮስፔስ እና ሮቦቲክስ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት (FARIS) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።
ስምምነቱንም ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩርያ (ዶ/ር ኢንጂ.) እና የFARIS መስራችና ስራ አስኪያጅ ወጣት ኤልያስ ይግዛው ፈርመውታል።
FARIS በወጣት ኢትዮጵያውያን መሃንዲሶችና የፈጠራ ባለሙያዎች የተቋቋመ የመረጃና ግንኙነት ቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።