ፖለቲካ
“ዲፕሎማሲ ትኩረት ይሰጠዋል…ድልድዩን ስንደርስ ግን እንሻገራለን” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ሱዳኖች የኢትዮጵያን ቅድመ ሁኔታ ተቀብለው “ይመለሳሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ አምባ. ዲና ገልጸዋል
በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለውን የድንበር ውጥረት በተመለከተ ከአል ዐይን ጋር ቆይታ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሱዳን መንግስት የወሰደው እርምጃ በሱዳን ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ያልጠበቀችው ክህደት እንደተፈጸመባትም አንስተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ላይ መሆኑን የገለጹት ቃል አቀባዩ ዲፕሎማሲ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልጸው ነገር ግን ድልድዩን ከደረስን እንሻገራለን ብለዋል፡፡