የአሜሪካ ኮንግረስ የትራምፕን ምርጫ ማሸነፍ በይፋ አረጋገጠ
በአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሀሪስ ሰብሳቢነት የተመራው የአሜሪካ ኮንግረስ የሪፐብሊካኑን ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፍ በይፋ አረጋግጧል
በፓርላማ በተረጋገጠው የመጨረሻ ድምጽ መሰረት ትራምፕ 312 ኢሌክቶራል ቮት፣ ሀሪስ ደግሞ 226 አግኝተዋል
የአሜሪካ ኮንግረስ የትራምፕን ምርጫ ማሸነፍ በይፋ አረጋገጠ።
በአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሀሪስ ሰብሳቢነት የተመራው የአሜሪካ ኮንግረስ የሪፐብሊካኑን ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፍ በይፋ አረጋግጧል።
በስብሰባው ከአራት አመት በፊት በምርጫ የተሸነፉት ትራምፕ ደጋፊዎች ወደ ኮፒቶል ሂል በማምራት ሁከት ከቀሰቀሱበት በተለየ መልኩ በሁለት ሳምንታት ውስጥ የትራምፕ በዓለ ሲመት እንዲፈጸም መንገድ ይከፍታል ተብሏል።
ትራምፕ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የ2020ውን ምርጫ የተሸነፉት የመራጮች ድምጽ ተሰርቆ መሆኑን ሲገልጹ መቆየታቸው እና በህዳር ወር በተካሄደው ምርጫ ሀሪስን እስከሚያሸንፉ ድረስ የ2024ቱ ምርጫ ሊጭበረበር ይችላል የሚል ስጋት ሲያንጸባርቁ ነበር።
በፈገግታ እና በአደባባይ ተስፈኛ ሆነው የሚታዩት ሀሪስ ለእያንዳንዱ ለትራምፕ እና ለራሳቸው ስቴት ኢሎክቶራል ቮት ሰርተፊኬት ሲሰጡ እጃቸውን አጣምረው ታይተዋል።
"ዛሬ በጣም ወሳኝ ቀን፤ ይህ መለመድ ያለበት ነው። የአሜሪካ ህዝብ ማወቅ ያለበት ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የዲሞክራሲ ዋነኛ ምሰሶ ነው" ሲሉ ሀሪስ በካፒሎል ሂል ለተሰባሰቡ ጋዜጠኞች ተኒግረዋል።
"ሀሪስ የአሜሪካ ዲሞክራሲ ጠንካራ ሆኖ የሚጠነክረው ለእሱ በምንዋጋው ልክ እንደሆነ በጽኑ አምናለሁ"።
ከአራት አመት በፊት የባይደንን የማሸነፍ ስነ ስርአት የመሩት ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ነበሩ።
በሀውስ ቻምበር ምክትል ፕሬዝደንት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርቲፊኬት የተሰጣቸው ሴናተር ዲጄ ቫንስም ተገኝተዋል። ቫንስ ከመቀመጫቸው ተነስተው አጠቃላይ የኢሎክቶራል ቮት ወይም የምርጫ ውጤት ሲገለጽ እጃቸውን በሀውስ ቻምበር ለነበሩ አባላት አውለብልበዋል።
"ኮንግረስ ድላችንን አረጋግጧል፤ በታሪክ ትልቅ ክስተት ነው"ሲሉ ትራምፕ ትሩዝ በተባለው ማህበራዊ ሚዲያቸው ሰኞ ጠዋት ጽፈዋል።
በፓርላማ በተረጋገጠው የመጨረሻ ድምጽ መሰረት ትራምፕ 312 ኢሌክቶራል ቮት፣ ሀሪስ ደግሞ 226 አግኝተዋል።