222 መቀመጫዎች ያሉትን ፓርላማ የትኛው ጥምረት ይቆጣጠረዋል የሚለው ከወዲሁ ቀልብን ስቧል
ሩቅ ምስራቃዊቷ ማሌዢያ ባካሄደችው ምርጫ ተፎካካሪዎቿ አንገት ለአንገት መያያዛቸው ተነገረ።
ሀገሪቱ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የተንጠለጠለ ፓርላማ ገጥሟታል የተባለ ሲሆን፤ ለዚህም ምክንያያቱ አብላጫ ድምጽ ያገኘ ፓርቲ መጥፋቱ ነው ተብሏል።
ሮይተርስ ግልጽ አሸናፊ ከሌለ የምጣኔ-ሀብት እድገቷ እያሽቆለቆለ እና የዋጋ ግሽበት እየናጣት ባለችው ማሌዢያ የፖለቲካ እርግጠኛ አለመሆን ሊቀጥል ይችላል ብሏል።
ዋና ዋና ፓርቲዎች አብላጫ ድምጽ አለማግኘታቸው የፓርቲዎቹ ጥምረት መንግስት ለመመስረት አብላጫ ህብረት መፍጠር ይኖርበታል።
የማሌዢያ ሕገ መንግሥታዊ ንጉሠ ነገሥት አብላጫ ድምጽ ማዘዝ ይችላል ብለው የሚያምኑትን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሾም ሥልጣን ስላላቸው ጣልቃ ሊገቡ ይችላሉ እየተባለ ነው።
የረዥም ጊዜ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንዋር ኢብራሂም ቅንጅት በቅዳሜው አጠቃላይ ምርጫ ብዙ መቀመጫ ማግኘቱን የምርጫ ኮሚሽኑ ውጤት አሳይቷል።
ሆኖም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሙህይዲን ያሲን ስልጣን ላይ ካለው የመንግስት ህዝባዊ ድጋፍ በማግኘቱት አስገራሚ የተባለ ድም ማግኘታቸው ታውቋል።
222 መቀመጫዎች ያሉትን ፓርላማ የትኛው ጥምረት ይቆጣጠረዋል የሚለው ከወዲሁ ቀልብን ስቧል።