ፈረንሳዊው አጥቂ ካሪም ቤንዜማ በጉዳት ከዓለም ዋንጫ ውጪ ሆነ
የ34 አመቱ የባሎንዶር አሸናፊው ቤንዜማ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም ቢያንስ ሶስት ሳምንታት ያስፈልጉታል
አሰልጣኝ ዴሻምፕስ “የቤንዜማ ከውድድሩ ውጪ መሆን ለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ትልቅ ጉዳት ነው” ብለዋል
የዓመቱ የዓለም ኮከብ ተጫዋችና ፈረንሳዊው አጥቂ ካሪም ቤንዜማ በጉዳት ምክንያት ከዓለም ዋንጫ ውጪ ሆነ፡፡
ካሪም ቤንዜማ ከውድድሩ ውጭ እንዲሆን የተገደደው ቅዳሜ በልምምድ ላይ ሳለ በግራ ጭኑ ላይ ያለው ጡንቻ በመጎዳቱ መሆኑን የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ጠቅሷል፡፡
በዚህም በዱሃ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ባደረገው የኤምአርአይ ምርምራ ውጤት መሰረት "ካሪም ቤንዜማ ከዓለም ዋንጫ ውጪ ነው" ሲል የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ኤፍኤፍኤፍ) አስታውቋል።
የ34 አመቱ የባሎንዶር አሸናፊው ቤንዜማ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም ሶስት ሳምንታት ያስፈልጉታል ተብሏል፡፡
በደረሰበት ጉዳት እጅጉን የተደናገጠው ቤንዜማ በኢንስታግራም ገጹ “በህይወቴ እንደዘሬ ምሽት ተስፋ ቆርጬ አላውቅም ነገር ግን ዛሬ ሁልጊዜ እንደማደርገው ስለ ቡድኑ ማሰብ አለብኝ ፤ እናም ቦታየ በተሸለ ብቃት ቡድኑን መርዳት ለሚችል ተጫዋች መተው እንዳለብኝ ይሰማኛል” በማለት ጽፏል፡፡
"ለሁሉም የድጋፍ መልዕክቶችዎ አመሰግናለሁ" ሲልም አክሏል፡፡
የፈረንሳዩ አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሻምፕስ በበኩላቸው “ይህን የዓለም ዋንጫ ትልቅ አላማው ላደረገው ካሪም በጣም አዝኛለው። ይህ ለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ትልቅ ጉዳት ቢሆንም በቡድኔ ሙሉ እምነት አለኝ። ይህን ትልቅ ፈተና ለመወጣት ሁሉንም ነገር እናደርጋለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አሰልጣኙ በቤንዜማ ምትክ ሶስት ኢንተርናሽናል ጎሎችን ላስቆጠረው የሞናኮው አጥቂ ዊሳም ቤን ዬደር እድል ሊሰጡ እንደሚችሉም ይገመታል፡፡
ቤንዜማ በ2014 የዓለም ዋንጫ የፈረንሳይ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የነበረ ቢሆንም በ2018 የዓለም ዋንጫ በፈረንሳይ አሸናፊነት አለመጫወቱ ይታወሳል።
የፈረንሳዩ አሰልጣኝ ዴሻምፕስ ባለፈው አመት በተካሄደው የአውሮፓ ሻምፒዮና ላይ ጥሪ አቅርበውለት በአራት ጎሎች የፈረንሳይ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡
ከቤንዜማ በተጨማሪ በቅርቡ እንደ ፖግባ እና ካንቴ የመሳሳሉ የመሃል ሜዳ ኮከቦች በጉዳት ምክንያት ከዚህ ዓለም ዋንጫ ውጭ መሆናቸው ለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ትልቅ ራስ ምታት እንደሆነ ይነገራል፡፡
ይህ ብቻ አይደለም አሰልጣኝ ዴስሻምፕስ ምርጡ የመሀል ተከላካዩ ራፋኤል ቫራኔ አውስትራሊያን ለመግጠም ብቁ መሆኑንና አለመሆኑን እርግጠኛ መሆን ይፈልጋሉ፡፡
የእግር ኳስ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ግን ቤንዜማ ባይኖርም ፈረንሳይ በምድቧ የሚገኙትን ሀገራት ለመግጠም ጠንካራ ብቃት አላት።
ምክንያቱም ደግሞ ፈረንሳይ እንደ የ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ኮከብ ካይሊያን ምባፔ ፣ የባርሴሎና ኦስማን ዴምቤሌ ፣ አንጋፋው አንትዋን ግሪዝማን እና በኦሊቪየር ጂሩድ የመሳሰሉ የፊት መስመር ተሰላፊዎች አሏትና ይላሉ ተንታኞቹ፡፡
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ጂሩድ ለፈረንሳይ 49 ጎሎችን ሲያስቆጥር፣ ግሪዝማን 42 እና የ23 አመቱ ምባፔ 28 ጎሎችን አስቆጥሯል እንዲሁም ዴምቤሌ በዚህ የውድድር አመት በስፔን ሊግ መሪ ባርሴሎና ጥሩ አቋም ላይ ይገኛል።
ፈረንሳይ ዛሬ በሚጀምረው የዓለም ዋንጫ አውስትራሊያ፣ ዴንማርክ እና ቱኒዚያ ባሉበት ቡድን ውስጥ መደልደሏ ይታወቃል፡፡ምክንያቱም ደግሞ ፈረንሳይ እንደ የ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ኮከብ ካይሊያን ምባፔ ፣ የባርሴሎና ኦስማን ዴምቤሌ ፣ አንጋፋው አንትዋን ግሪዝማን እና በኦሊቪየር ጂሩድ የመሳሰሉ የፊት መስመር ተሰላፊዎች አሏትና ይላሉ ተንታኞቹ፡፡
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ጂሩድ ለፈረንሳይ 49 ጎሎችን ሲያስቆጥር፣ ግሪዝማን 42 እና የ23 አመቱ ምባፔ 28 ጎሎችን አስቆጥሯል እንዲሁም ዴምቤሌ በዚህ የውድድር አመት በስፔን ሊግ መሪ ባርሴሎና ጥሩ አቋም ላይ ይገኛል።
ፈረንሳይ ዛሬ በሚጀምረው የዓለም ዋንጫ አውስትራሊያ፣ ዴንማርክ እና ቱኒዚያ ባሉበት ቡድን ውስጥ መደልደሏ ይታወቃል፡፡