ዶናልድ ትራምፕ ለ2024 የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ በይፋ አወጁ
“አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት እጩ መሆኔን አስታውቃለሁ”- ትራምፕ
በፕሬዝዳንትነት የምረጡኝ ዘመቻዎች ረጅም ጊዜ በመመደብ ለምትታወቅ ሀገር የትራምፕ ዜና ከጀርባው ፍላጎት አለው ተብሏል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ በ2020 ምርጫ ከተሸነፉ በኋላ ዳግም እንደሚወዳደሩ አሳውቀዋል።
በአሜሪካ ድምጽ አሰጣጥ ታማኝነት ላይ የማያቋርጥ ትችት ሲሰነዝሩ የከረሙት ትራምፕ በፈረንጆቹ በ2024 የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ለማግኘት ትናንት ማክሰኞ ማክሰኞ በይፋ እጩነታቸውን አውጀዋል።
ከዲሞክራቱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋር የድጋሚ ፍጥጫ በመፈለግ ትራምፕ በፍሎሪዳ ተወዳዳሪነታቸውን ያሳወቁት ትራምፕ፤ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ሪፐብሊካኖች ያሰቡትን ያህል መቀመጫዎች ማሸነፍ በተሳናቸው ማግስት ነው።
ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀ ንግግር ያደረጉት ትራምፕ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን በአሜሪካ ባንዲራ ባጌጠ አዳራሽ ውስጥ አነጋግረዋል።
“አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ዛሬ ምሽት ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት እጩ መሆኔን አስታውቃለሁ” ሲሉ ትራምፕ ለተሰበሰበው ህዝብ፣ የቤተሰብ አባላት፣ ለጋሾች እና የቀድሞ ሰራተኞችን ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ትራምፕ ፕሬዝዳንት የባይደን ላይ ትችት በመሰንዘር እሳቸው ዋይት ሀውስ በነበሩበት ጊዜ ያከናወኗቸውን የፖሊሲ ስኬቶችን በመገምገም ውጭ ስም በመጥራት ከነቀፌታ መቆጠባቸው ተነግሯል።
“ከሁለት አመት በፊት ታላቅ ህዝብ ነበርን እናም በቅርቡ እንደገና ታላቅ ህዝብ እንሆናለን” ሲሉ የሚታወቁበትን መልዕክት ተናግረዋል።
ትራምፕ ስደተኞችን በማውገዝ፣ “እየተመረዝን ነው” ያሉ ሲሆን የአሜሪካ ከተሞችን በወንጀል የተጨማለቁ “የደም ማጠራቀሚያዎች” በማለት የታወቀ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።
በፈረንጆቹ በ2024 ክረምት የሪፐብሊካን እጩ በይፋ የሚመረጡ ሲሆን፤ የትራምፕ እወጃ ከወትሮው አሰራር የቀደመ ነው ተብሏል።
በፕሬዝዳንትነት የምረጡኝ ዘመቻዎች ረጅም ጊዜ በመመደብ ለምትታወቅ ሀገር የትራምፕ ዜና ከጀርባው ፍላጎት የያዘ ነው ተብሎለታል። የፍሎሪዳ ገዥ ሮን ዴሳንቲስ ወይም የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩነት መጠበቅ ሌሎች ተፎካካሪዎችን ከጨዋታው ለማስወጣት ያላቸውን ፍላጎት ያሳያል ተብሏል።