ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት የነበረችው ሞሮኮ በደቡብ አፍሪካ 2-0 ተሸንፋ ሩብ ፍጻሜውን ሳትቀላቀል ቀርታለች
ሞሮኮም ሳትጠበቅ ከውድድሩ ተሰናብታለች።
ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት የነበረችው ሞሮኮ በደቡብ አፍሪካ 2-0 ተሸንፋ ሩብ ፍጻሜውን ሳትቀላቀል ቀርታለች።
እምብዛም ግምት ያልተሰጣት ደቡብ አፍሪካ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።
የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ያለምንም ግብ የተጠናቀቀ ሲሆን በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ በ57ኛው ደቂቃ ላይ ማጎፖ ባስቆጠራት ግብ አማካኝነት ደቡብ አፍሪካ መምራት ቻለች።
የግቧን መቆጠር ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ውስጥ የገባው የሞሮኮ ቡድን አቻ ለመሆን የሚያስችል ግብ ለማግኘት ሙከራዎች ቢያደርግም ወደ ግብ መቀየር አልቻለም።
የሞሮኮው አጥቂ አሽራፍ ሀኪሚ የ90 ደቂቃው ጨዋታ ሊጠናቀቅ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ፍጹም ቅጣት ምት በመሳት የሚያስቆጭ እድል አምክኗል።
ሀኪሚ ግቧን ማስቆጠር ቢችል ኖሮ የሞሮኮ ቡድን ጨዋታውን እንዲቀይር ሊያደርገው ይችል ነበር።
በጨዋታ የጭማሪ ደቂቃ ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ አጥቂ ቴቦ ሞኮይና ሁለተኛዋን ግብ በማስቆጠሩ የሞሮኮን የአቻነት ተስፋ እንዲሟጠጥ አደረገው።
ይባስ ብሎ የሞሮኮው አማካኝ ተጨዋታ አምራባት በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
በዚህ ጨዋታ የተሻለ ለውጥ ሊያመጡ ይችሉ ነበር የተባሉት ዛይች እና ሶፊያን ቡፎን በጉዳት ምክንያት ሳይሰለፉ ቀርተዋል።
በኳታሩ የአለም ዋንጫ ታላላቅ ቡድኖችን በማሸነፍ አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሞሮኮ ሽንፈት ያልተጠበቀ ነው።
ሞሮኳውያን ደጋፊዎች በሽንፈቱ አንገታቸውን ደፍተዋል፣ መቀበልም አቅቷቸዋል።
በሌላ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ማሊ ቡርኪናፋሶን 2-1 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቅላለች።
የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በብዙዎች ዘንድ ያልተጠበቁ ውጤቶችን እያስተናገደ ይገኛል።በውድድሩ ረጅም ርቀት ይሄዳሉ የሚል ግምት የተሰጣቸው የውድድሩ 2019 አሸናፊዋ አልጀሪያ፣ የ2021 አሸናፊዋ ሴኔጋል፣ አልጀሪያ እና ጋና ከሩብ ፍጻሜው በፊት ተንጠባጥበዋል።