የኮፕ28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን አልጃቢር ከሴኔጋል አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ጋር መከሩ
ሁለቱ መሪዎች በአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተገናኝተው መክረዋል
የዘንድሮው የተመድ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የፊታችን ሕዳር በዱባይ ይካሄዳል
የኮፕ28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን አልጃቢር ከሴኔጋል አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ጋር መከሩ፡፡
የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዝዳንት እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አልጃቢር በአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
19ኛው የአፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች ጉባኤ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት እድሎችን መጠቀም እና ትብብርን ማጎልበት" በሚል ሀሳብ በአዲስ አቡባ ተካሂዷል።
ዶክተር አልጃቢር ከጉባኤው ጎን ለጎንም ከሴኔጋል አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር እና ከአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ የሚኒስትሮች ጉባኤ ሊቀመንበር ከሆኑት አሊየን ንዶዬ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ጎግል የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የተጀመረውን ጥረት በማገዝ ላይ መሆኑ ተገለጸ
ሁለቱ መሪዎች በአፍሪካ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት የጤና፣ ምግብ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት እና ማላመድ ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ስላለው ጉዳጥ መጠን፣ የካሳ እና ጉዳት መቀነስ በሚቻልባቸው የመፍትሄ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል ተብሏል፡፡
የኮፕ28 አለም አቀፍ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ እየተጎዱ ካሉ አህጉራት መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ዶክተር አል ጃቢር አክለውም የፊታችን ህዳር በዱባይ የሚካሄደው ኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለአፍሪካ እና ለቀሪ አህጉራት የሚጠቅም ውሳኔ የሚተላለፍበት እንደሚሆንም አክለዋል።