ኮፕ28 ለአለም በትብብር መፍትሄ ለማምጣት የሚያስችል መድረክ ነው- የአፍሪካ ባለስልጣናት
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት የተካሄደው የተመድ የአየር ንብረት ስብሰባ ወይም ኮፕ28 በትናንትናው እለት ተጠናቋል
በአፍሪካ ዘላቂ የንግድ ፎረም ላይ የተሳፉ ባለስልጣናት እና ተሳታፊዎች ኮፕ28 ሀገራት በአንድ ላይ በመምጣት ከባድ የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር እንዲዋጉት ይረዳል ብለዋል
የአፍሪካ ባለስልጣናት የኮፕ28 ለአለም በትብብር መፍትሄ ለማምጣት የሚያስችል መድረክ ነው ብለዋል።
ከኮፕ 28 ስብሰባ ጎን ለጎን በአፍሪካ ዘላቂ የንግድ ፎረም ላይ የተሳፉ ባለስልጣናት እና ተሳታፊዎች ኮፕ28 ሀገራት በአንድ ላይ በመምጣት ከባድ የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር እንዲዋጉት ይረዳል ብለዋል።
ተሳታፊዎቹ እንደገለጹት በአፍሪካ ዘላቂ የሆነ የንግድ ስራ ማካሄድ እና በኮፕ28 የተቀመጡ የአየር ንብረት ቅነሳ ግቦችን ማሳከት የማይነጣጠሉ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይ የማላዊ የኢነርጂ ሚኒስትር ኢብራሂም ሞታላ አፍሪካ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ብዙ እድሎች እንዳሏት የገለጹ ሲሆን የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ የዳይሬክሮች ቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ቤነዲክት ኦኪ ኦራማህ ደግሞ ያሉትን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች አስረድተዋል።
'የአፍሪካ 50' ፕላትፎርም ዋና ስራ አስፈጻሚ አላይን ኡቡብሲ እንተናገሩት ፕላትፎርሙ በአፍሪካ አስተማማኝ መሰረልማት እንዲዘረጋ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት የተካሄደው የተመድ የአየር ንብረት ስብሰባ ወይም ኮፕ28 በትናንትናው እለት ተጠናቋል።
በስብሰባው ከ198 ሀገራት በላይ የተካፈሉ ሲሆን በርካታ ስምምነቶች ደርሰዋል።