ሩሲያ ከኢራን ጋር "ትልቅ ስምምነት" ልትፈራረም መሆኗን ገለጸች
የኢራን ባለስልጣናት ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ወታደራዊ ትብብር በየቀኑ እየጨመረ ነው ብለዋል
ሩሲያ እንደገለጸችው የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ያለውን ስምምነት በማፋጠን ጉዳይ በስልክ ተወያይተዋል
ሩሲያ ከኢራን ጋር "ትልቅ ስምምነት" ልትፈራረም መሆኗን ገለጸች።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሩሲያ እና ኢራን "አዲስ ትልቅ ኢንተርስቴት"ስምምነት ለመፈራረም የሚያስፈልጉ ስራዎች እያፋጠኑ መሆናቸውን ገልጿል።
አሜሪካ በስጋት የምትመለከተው የሩሲያ እና ኢራን የፖለቲካ፣ የንግድ እና ወታደራዊ ግንኙነታቸው በጨመረበት ወቅት የሚፈረመው ይህ ስምምነት በምን ጉዳዮች ላይ እንደሚሆን ግልጽ አልተደረገም።
ሩሲያ እንደገለጸችው የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ያለውን ስምምነት በማፋጠን ጉዳይ በስልክ ተወያይተዋል።
ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲ ጋር በክሬሚሊን ለአምስት ውይይት አድርገዋል።
መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን የሩሲያውን ፑቲን በሩቅ ምስራቅ እንዳገኘው ሰሜን ኮሪያ ሁሉ በዩክሬን ጦርነት ለሩሲያ ድሮን ሰጥታለች የምትባለው ኢራን የአሜሪካ ዋነኛ ጠላት ነች።
ክሬሚሊን ባለፈው ወር ከኢራን በወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች እና በሌሎች ዘርፎች ትብብር እንደምታደርግ ገልጾ ነበር።
የእስራእሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ባለፈው ቅዳሜ ለፑቲን ደውለው፣ ሩሲያ ከኢራን ጋር እያደረገችው ያለው ትብብር አደገኛ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገለጸውላቸዋል።
የኢራን ባለስልጣናት ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ወታደራዊ ትብብር በየቀኑ እየጨመረ ነው ብለዋል።