በእስራኤል እየተደበደበች ያለችው ጋዛ የረሀብ አደጋ አንዣቦባታል ተባለ
እስራኤል ትናንት ሌሊቱን ባደረገችው ጥቃት ከግብጽ ጋር በምትዋሰነው በደቡብ ጋዛ በምትገኘው የራፋ ከተማ 22 ሰዎች ተገድለዋል።
ተመድ ለረሀብ አደጋ ለተጋለጡት የጋዛ ነዋሪዎች የሚደረገው የእርዳታ ስርጭት ባለው ከባድ ጦርነት ምክንያት በአብዛኛው መቆሙን ገልጿል
የከፍተኛ የረሀብ አደጋ ያንዣበበባት ጋዛ በእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች እና ታንኮች ከፍተኛ ድብደባ እየደረሰባት ይገኛል።
ተመድ ለረሀብ አደጋ ለተጋለጡት የጋዛ ነዋሪዎች የሚደረገው የእርዳታ ስርጭት ባለው ከባድ ጦርነት ምክንያት በአብዛኛው መቆሙን ገልጿል።
እስራኤል ትናንት ሌሊቱን ባደረገችው ጥቃት ከግብጽ ጋር በምትዋሰነው በደቡብ ጋዛ በምትገኘው የራፋ ከተማ 22 ሰዎች ተገድለዋል።
የነፍስ አድን ሰራተኞች የጥቃቱ ሰላባ የሆኑ ተጨማሪ ሰዎች በመፈለግ ላይ ናቸው።
በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተቀሰቀሰው እና ሁለት ወራትን ያስቆጠረውን ጦርነት ለማስቆም በተመድ የጸጥታው ምክርቤት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ አሜሪካ በመቃወሟ ሳይጸድቅ ቀርቷል።
15 አባላት ካሉት የጸጥታው ምክርቤት ውስጥ 13ቱ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የደገፉ ሲሆን እንግሊዝ ድምጽ ከመስጠት ታቅባለች።
አሜሪካ የውሳኔ ሀሳቡን የተቃወመችው ተኩስ አቁሙ የሚጠቅመው ሀማስን ብቻ ነው በሚል ምክንያት ነው።
ለአሜሪካ እና ለእስራኤል ተኩስ አቁም ማለት ሀማስ ሌላ ጥቃት ለመሰንዘር እንዲዘጋጅ ጊዜ መስጠት ነው።
በጋዛ ያለው የሰብአዊ ቀውስ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱ የረብ አደጋ ያስከትላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
በእስራኤል መጠነሰፋ ጥቃት እስካሁን ከ18ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።