ኮፕ28 በ12 ቀን ጉዞው ከ83 ቢሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ቃል ተገብቶበታል
12ኛ ቀኑን የያዘው ኮፕ28 በርካታ ስምምነቶች የተደረሱበት የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ሆኗል።
በጉባኤው በጤና፣ በግብርና፣ በምግብ ስርአት እንዲሁም በታዳሽ ሃይል ልማት ከ11 በላይ የቃልኪዳን ሰነዶች የተፈረሙበት ጉባዔው ከ83 ቢሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ቃል የተገባበት ጉባኤ መሆንም ችሏል።
ሀገራት በዱባዩ ጉባኤ ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ 792 ሚሊየን ዶላር ለማዋጣትም ቃል መግባታቸውም የሚታወስ ነው።
3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያለው የ”ግሪን ክላይሜት ፈንድ” ለማቋቋምም ቃል ተገብቷል።
የተለገሱና ቃል የተገቡ የገንዘብ ድጋፎችን ዝርዝር ይመልከቱ፤