ኮፕ28 ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳቶችን ለመቀነስ ልዩ እድል እንደሆነ ተገለጸ
መድረኩ የሀገራት መሪዎች እና ባለሙያዎችን ፊት ለፊት እንዲገናኙ ያደረገ ነበር ተብሏል
በዱባይ እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 ጉባኤ የመጨረሻ ቀኑ ላይ ይገኛል
ኮፕ28 ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳቶችን ለመቀነስ ልዩ እድል እንደሆነ ተገለጸ፡፡
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ 12ኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ ምድራችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስ ጉዳትን መቀነስ የሚያስችሉ ምክክሮች እና ውይይቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡
ከ11 ቀናት በፊት በተባበሩት አረብ ኢምሬት መዲና ዱባይ የተጀመረው ኮፕ28 ጉባኤ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ የሚችሉ ዓለም ሀገራት እና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎች ባንድ ላይ ተገናኝተውበታል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ ምድራችንን ከከፋ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎች መጠበቅ የሚያስችሉ በርካታ ውሳኔዎች እንደተወሰኑበት ተገልጿል፡፡
ለአብነትም ታዳጊ ሀገራት በየጊዜው የሚደርሱ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችለው የአየር ንብረት ፈንድ ዋነኛው ሲሆን ይህ ተቋም በዓመት 100 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሰበስብ አስታውቋል፡፡
ይህ ውሳኔ ለዓመታት ሲንከባለል የመጣ ሲሆን ውሳኔ ሰጪዎች እና የውሳኔ ሃሳብ ሰጪዎች በአንድ ስፍራ በመገናኘታቸው ዘንድሮ ወደ ተግባር ለመቀየር በቅቷል፡፡
ሌላኛው የዚህ ጉባኤ ስኬት የተደረገው ወደ ካቢ አየር ከፍተኛ ጋዝ በመላክ የሚታወቁት የጋዝ አምራች ኩባንያዎች በካይ ጋዝን ለመቀነስ ወደ ስምምነት መምጣታቸው ነው፡፡