ታሪካዊ ስምምነት የተፈረመት የኮፕ28 የአየር ንብረት ስብሰባ
ይህ ስብሰባ ለመጀመሪያ ጊዜ ከነዳጅ ዘይት እና ጋዛ ወደ ታዳሽ ሽግግር እንዲደረግ ስምምነት ላይ ተደርሶበታል
የኮፕ28 ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃብር በስብሰባ ያልተጠበቀ ስኬት ተመዝግቧል ብለዋል
ታሪካዊ ስምምነት የተፈረመት የኮፕ28 የአየር ንብረት ስብሰባ
የኮፕ28 ስብሰባ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ጠንክሮ በመስራት፣በቁርጠኝነት እና በተገኙ ስኬቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች ለሚያስጨንቋቸው ሰዎች ልዩ መሆኑን አስመስክሯል።
በዛሬው እለት የኮፕ28 ስብሰባን እየተካፈለ ካለው የአውሮፖ ህብረት በተጨማሪ የ197 ሀገራት ተወካዮች አለምን በትክክለኛው መስመር ላይ የሚያስቀምጥ ታሪካዊ "የዩኤኢ ስምምነት" ላይ ደርሰዋል።
ሀገራት ከነዳጅ እና ጋዝ የኃይል ምንጭ በሂደት ወደ ታዳሽ ኃይል ለመሸጋገር ነው የተስማሙት።
የኮፕ28 ስብሰባ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ወሳኝ ምዕራፍ የሚሆነውን ያልተጠበቀውን እና ታሪካዊውን ስምምነት አጽድቀዋል።
በስምምነቱ መሰረት ሀገራት የአለም የሙቀት መጠን 1.5 ዲግሪ ሴልሼስ እንዳይበልጥ ጥረት ያደርጋሉ።
ስምምነቱ የተደረሰው ለአመት በዘለቀ ድርድር እና በኮፕ28 ፕሬዝደንት ጥረት ነው።
ስምምነቱ በማድግ ላይ ያሉ እና ትላልቅ ኢኮኖሚዎችን የሚጠቅም እንዲሁም አለምአቀፍ የአየር ንብረት ግቦች እንዲሳኩ የሚያስችል ነው።
በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን "የሎስ ኤንድ ዳሜጅ" ፈንድን ወደ ስራ ለማስገባት ታሪካዊ የተባለ ስምምነት መደረሱ ይታወሳል። ስብሰባው በቆየበት 13 ቀናት ውስጥ የአየር ንብረትን ለመዋጋት የሚያስችል 85 ቢሊዮን ዶላር መሰብሰብ ተችሏል።
ኮፕ28 መሪዎች ቃል ለመግባት እና ዲክላሬሽንስ ለማጽደቅ ታሪካዊ መግባባት ላይ የደረሱበት ስብሰባ ነው።
የአረብ ኢምሬትስ የኢንዱስትሪ እና የአድቫንስድ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኮፕ28 ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃብር በስብሰባ ያልተጠበቀ ስኬት ተመዝግቧል ብለዋል።
"በዱባዩ ኮፕ28 የሆነ የተለየ ነገር እየተከሰተ እንደሆነ መስማማት እንችላለን። ተሳታፊዎቹ በአንድነት ቆመዋል"
ይህ ስብሰባ ለመጀመሪያ ጊዜ ከነዳጅ ዘይት እና ጋዛ ወደ ታዳሽ ሽግግር እንዲደረግ ስምምነት ላይ ተደርሶበታል።