ሀገራት ታሪካዊ ስለተባለው የአየር ንብረት ስምምነት ዙሪያ ምን አሉ?
በኮፕ28 ስብሰባ 198 ሀገራት ተሳትፈዋል
ሀገራት አስከፊውን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ለመከላከል ነዳጅን ከመጠቀም ወደ ታዳሽ ኃይል ለመሸጋገር ስምምነት ላይ ደርሰዋል
ሀገራት ታሪካዊ ስለተባለው የአየር ንብረት ስምምነት ዙሪያ ምን አሉ?
በአረብ ኢምሬትስ በተካሄደው የኮፕ28 ስብሰባ ሀገራት አስከፊውን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ለመከላከል ነዳጅን ከመጠቀም ወደ ታዳሽ ኃይል ለመሸጋገር ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ስለስምምነቱ የተሰነዘሩት የተወሰኑት ግበረመልሶች እነዚህ ናቸው
የአሜሪካ የአየር ንብረት ተወካይ ጆን ኬሪ፦
"ሁሉም ወደ አንድ የመጣበት የትብብር መንፈስ አስገርሞኛል"
የዴንማርክ የአየር ንብረት እና ኢነርጅ ሚኒስትር ጆርገንሰን፦
"ነዳጅ በምታመርት ሀገር ላይ ነው የቆምነው፣ በነዳጅ አምራች ሀገራት ተከበን፣ከነዳጅ እና ጋዝ እንላቀቅ የሚል ውሳኔ ወስነናል"
የትናንሽ ደሴት ሀገራትን የወከሉት የሳሞኣ ተወካይ አኔ ራዝሙዘን "በመሉ ድምጽ ውሳኔ ላይ መደረሱ አስገርሞናል ብለዋል"።
የባንግላንዲሽ የአየር ንብረት ተወካይ ሳበር ሆሴን ቾውድኸሪይ፦
"የአየር ንብረት ለውጥን መቀነስ የሞት እና የህይወት ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ አንደራደርም፤ በህይወታችን እና በመኖሪያችን ላይ ድርድር የለም"
የካናዳ የአየር ንብረት ተወካይ፦
"ኮፕ28 ታሪካዊ ስምምነት ላይ ደርሷል። ለአጭር ጊዜ እርምጃዎች እድሎችን የሚሰጥ እና ከ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ጋር የሚጣጣም የአረንጓዴ ሸግግር ለማድረግ ያስችላል"
የቻይና ምክትል የአካባቢ ሚኒስትር ዛሆ ይንግሚን፦
"ያደጉ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይናወጥ ኃላፊነት አለባቸው"
የሲንጋፖር የአካባቢ ሚኒስቴር ግሬስ ፉ "ውጤቶቹን የስምምነት አካል አድርገን መውሰድ አለብን። በድርድር ውስጥ ተደራዳሪዎች ቡዙ ጊዜ በራሳቸው ፍላጎት ላይ ያተኩራሉ። እንደ ማብቃት ወይም 'ፌዝ ከውት' የመሳሰሉ ቃላት ችግር ይሆናል። ወሳኙ ነገር ይዘቱ እና አላማው ነው" ብለዋል።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት አል ጎሪ፦
"ለአየር ንብረት ቀውስ ዋናው ምክንያት ነዳጅ ነው ተብሎ በኮፕ28 ስብሰባ ላይ ከስምምነት መደረሱ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ነገርግን ይህ ጥቂት እና ለረጅም ጊዝ ሲጠበቅ የቆየ ነው። የነዳጅ አምራች ሀገራት ተጽዕኖ አሁንም ቢሆን በመጨረሻው ስምምነት ላይ በነበሩ ክፍተቶች ይታያል"።
"ይህ ስምምነት የነዳጅ ዘመን የመጨረሻ መጀመሪያ መሆኑ የሚታየው በአተገባበሩ ይወሰናል"