ሕንድ ለኮፕ28 የአየር ንብረት ጉባኤ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች
በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረው የኮፕ28 ጉባኤ በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት ይካሄዳል
ኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የፊታችን ሕዳር በአቡዳቢ ይካሄዳል
ሕንድ ለኮፕ28 የአየር ንብረት ጉባኤ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች።
የዓለማችንን ቀዳሚ የህዝብ ብዛት ያላት ሕንድ የተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት ለሚካኬደው የዓለም አየር ንብረት ጉባኤ ስኬት ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጻለች።
የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ራሬንድራ ሞዲ ከኮፕ28 የአየር ንብረት ጉባኤ ፕሬዝዳንት እና ከኢንዱስትሪ ሚንስትር ዶክተር ሱልጣል አልጃቢር ጋር ተወያይተዋል።
በአቡዳቢ በተካሄደው በዚህ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለኮፕ28 ጉባኤ ታሪካዊ እና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሕንድ ድጋፍ ታደርጋለች ተብሏል።
በየዓመቱ የሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በተለያዩ ሀገራት ይካሄዳል።
የዘንድሮውን ማለትም ኮፕ28 ጉባኤን የምታስተናግደው አረብ ኢምሬት ስትሆን በመድረኩም የተለያዩ የዓለም ሀገራት ይሳተፉበታል።
ጉባኤው እየጨመረ ለመጣው የአለም አየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ማፈላለግ የዚህ ጉባኤ ዋነኛ አላማ እንደሆነም ተገልጿል።
የጉባኤው አስተናጋጅ የሆነችው አረብ ኢምሬትም አስቀድማ ዝግጅት በማድረግ ላይ ስትሆን ከተለያዩ ሀገራት ጋር እየመከረችም ትገኛለች።
ባሳለፍነው ሳምንት የተባበሩት አረብ ኢምሬትን የጎበኙት የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ጉባኤው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በውጭ ግንኙነት በኩል ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል።
ሕንድ ለአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት መስጠቷን የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ በተለይም ለጸሀይ ብርሀን ሀይል ልማት፣ ለአደጋ መከላከል እና መላመድ እና ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቅ ጋዝን መቀነስ ትኩረት መስጠቷንም አክለዋል።