በኮፕ28 የተሳታፊዎች ክብረወሰን
በ28ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው
የኮፕ28 ተሳታፊዎች በግብጽ ሻርም አልሼክ ከተመዘገበው በእጥፍ ይበልጣሉ
በአረብ ኤምሬትስ ዱባይ እየተካሄደ የሚገኘው 28ኛው የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በተሳታፊዎች ብዛት ክብረወሰን ይዟል።
የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በኮፕ28 ጉባኤ በአካል ለመሳተፍ 97 ሺህ 372 ሰዎች ተመዝግበዋል፤ 3 ሺህ 74 ሰዎችም ጉባኤው ላይ በበይነ መረብ ተሳትፈዋል።
ይህም የጉባኤውን ተሳታፊዎች ቁጥር 100 ሺህ 446 በማድረስ በመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታሪክ ቀዳሚው ሆኖ ተመዝግቧል።
በግብጽ ሻርም አልሼክ በተካሄደው ጉባኤ 50 ሺህ፤ በ2021 በስኮትላንድ ግላስጎ በተካሄደው ኮፕ26 ደግሞ 38 ሺህ ተሳታፊዎች መመዝገባቸውን የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ ያወሳል።