የ83 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ቃል የተገባበት ኮፕ28
በዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባኤ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ድጋፍ እያደረጉ ነው
11 የአየር ንብረት ለውጥን ለሚቀንሱ ስራዎች የፋይናንስ ድጋፍ የማድረግ ስምምነቶች ተደርሰዋል
በአረብ ኤምሬትሷ ዱባይ እየተካሄደ የሚገኘው 28ኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ዛሬ ስምንተኛ ቀኑን ይዟል።
ጉባኤው በመጀመሪያ አምስት ቀናት ቆይታው ብቻ የ83 ቢሊየን ዶላር ቃል የተገባበት በመሆንም ታሪካዊ ሆኗል።
ለአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ስራዎች ኤምሬትስ ያቋቋመችውን የ30 ቢሊየን ዶላር ፈንድ ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት የድጋፍ ቃል መግባታቸውን የጉባኤው አዘጋጆች ተናግረዋል።
በጉባኤው እስካሁን የአየር ንብረት ለውጥ ለሚያስከትለው ችግር ምላሽ ለመስጠትና ለታዳሽ ሃይል ልማት 11 የቃልኪዳን ሰነዶች ተፈርመዋል።
በቀሪዎቹ አምስት ቀናትም በርካታ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ድጋፍ ለማድረግ ቃል እንደሚገቡ ይጠበቃል።
እስካሁን ቃል የተገባውን ድጋፍ በዝርዝር ይመልከቱ፦