አረብ ኢምሬት ለተጋላጭ ማህበረሰብ የውሀ ደህንነት 150 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች
ሀገሪቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ድጋፍ 5 ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ እንደምታደርግ አስታውቃለች
28ኛው የተመድ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በዱባይ በመካሄድ ላይ ይገኛል
አረብ ኢምሬት ለተጋላጭ ማህበረሰብ የውሀ ደህንነት 150 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር ይመክራል፡፡
ይህ ጉባኤ በተመድ አባል ሀገራት እየተዟዟረ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት በዱባይ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ካሳለፍነው አርብ ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን የጉባኤው አዘጋጅ የሆነችው አረብ ኢምሬት ተጨማሪ ድጋፎችን እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡
ሀገሪቱ ላልተረጋጉ ሀገራት የውሃ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ 150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከግል ባለሀብቶች እና የንግድ ኩባንያዎች 18 ቢሊዮን ድርሃም ወይም 5 ቢሊዮን ዶላር በመሰብሰብ ለአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ድጋፍ እንደምታውልም ገልጻለች፡፡
በዱባይ እየተካሄደ ባለው 28ኛው የተመድ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የ200 ሀገራት መሪዎች፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎች፣ የተቋማት መሪዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
የአፍሪካ ተደራዳሪ ቡድን የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ፈንድ መቋቋሙን አወደሰ
አረብ ኢምሬትን ጨምሮ የተለያጠዩ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ፈንድ ያዋጡት ገንዘብ 400 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል፡፡
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ ሀገራቸው ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄዎች የ30 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ማቋቋሟን ከትናንት በስቲያ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ለአየር ንብረት መፍትሄዎች ፈንድ የተቋቋመው የአየር ንብረት ፋይናንስ ክፍተቱን ለመሙላትና እና ገንዘቡ በተገቢው መልኩ ተደራሽነቱን ለማመቻቸት ነው ብለዋል።