የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃን ማፋጠን ለኢንቨስትመንትና ዘላቂ እድገት እድል ይፈጥራል- የኮፕ-28 ፕሬዝዳንት
ዓለም በፓሪስ ጉባኤ ቃል-ኪዳኖች ካልተገበረ የአየር ንብረት ለውጥ መዘዙ ከባድ እንደሚሆን ይገለጻል
የፓሪስ ስምምነት ግቦችን ለማሳካት ዓለም ወደ ትክክለኛው እንድተመለስ እንደሚረዳ ገልጸዋል
የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃን ማፋጠን ለኢንቨስትመንትና ዘላቂ እድገት እድል እንደሚፈጥር የኮፕ-28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን አልጃበር ገለጹ።
በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ሲካሄድ የነበረው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-28) የባለድርሻ አካላት ስብሰባ ተጠናቋል።
የአረብ ኢምሬት ኢንዱስትሪ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሁም የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢር በስብሰባው ላይ የባለ ድርሻ አካላት ስብሰባው ለአየር ንብረት ርምጃ ልዩ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።
- አረብ ኢሚሬትስ ለአየር ንብረት ለውጥ የሚደረገው ጥረት በእጥፍ እንዲያድግ ጠየቀች
- የኮፕ- 28 ፕሬዝዳንት ሱልጣን አል ጃበር ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ማክሮን ጋር ተወያዩ
ስብሰባው የፓሪሱን ስምምነት ግቦች በመተግበር ረገድ የተገኘውን እድገት ለመገምገም የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ስበሰባ መሆኑንም እታውቀዋል።
አረብ ኤሚሬቶች የኮንፈረንሱ ፕሬዝዳንትነቷ በአየር ንብረት ርምጃው ላይ መሻሻል ለማምጣት፣ ዓለም አቀፍ መግባባት ላይ ለመድረስ እና ወደፊት የአየር ንብረት እርምጃን በተመለከተ ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ለማቅረብ እንደምትሰራም አስታውቀዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ስር ነቀል ለውጥ ማመውጣት በትሪሊዮን የሚቆጠር ዶላሮችን በማፍሰስ እድገትን እና ብልጽግናን በሚያጎለብት መልኩ ኢንቨስት ለማድረግ እና አዳዲስ የስራ እድሎችን ለመፍጠር አስተዋፅኦ ይኖረዋል ሲሉም ተናግረዋል።
አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና ልማት ባንኮች ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ ቡድኖችን ፍላጎት ለማሟላት በሚቀርቡ የመፍትሄ ሃሳብ መሳተፍ አለባቸው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-28) ፕሬዝዳንት የሆነችው አረብ ኢምሬትስ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚሰሩ ስራዎች ሁሉም ሰው ባሳተፈ መልኩ ውጤታማ እንዲሁም በጋራ ዓለም አቀፋዊ ትብብር እንዲደረግም ጥሪ አቅርባለች።