ጀርመን እና አረብ አሚሬትስ በኮፕ-28 ዝግጅት ዙሪያ በትብብር ሊሰሩ ነው
ጀርመን እና ዩኤኢ በኢነርጂ መስክ የሚያደርጉት ትብብር ወደ የሃይድሮጅን ስርአቶችን ማቀናጀት ከፍ ብሏል
ጀርመን፤ “የዓለም ሙቀትን በ1.5 ዲግሬ ሴልሺዮስ እንዲገደብ ከማድረግ ውጪ ሌላ መንገድ የለም" ብላለች
ጀርመን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጋር በኮፕ-28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያ በትብብር እንደሚሰሩ የጀርመን ኢኮኖሚ እና የአየር ንብረት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡
ቃል አቀባዩ ለ"አል አይን ኒውስ" እንደተናገሩት "የኮፕ-28 የአየር ንብረት ልውጥ ጉባኤን ዝግጅት በመተለከተ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጋር ገንቢ ምክክር እያደረግን ነው” ብለዋል፡፡
ዝግጅቱን በተመለከተ ይበልጥ ለመነጋገር የጀርመን የአየር ንብረት ፖሊሲ ኮሚሽነር ጄኒፈር ሞርጋን በዚህ ሳምንት ወደ አቡዳቢ እንደሚያቀኑም ጭምር ተናግረዋል፡፡
ሞርጋን በቆይታቸው ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የኢንዱስትሪ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና ከአየር ንብረት ለውጥ ልዩ መልዕክተኛ ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበርን እና ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የአየር ንብረት ለውጥ ና የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ሜሪየም አል ሙሃይሪን ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ገልጸዋል ቃል አቀባዩ፡፡
በተጨማሪም የጀርመን የአየር ንብረት ፖሊሲ ኮሚሽነር ጄኒፈር ሞርጋን ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ተደራዳሪ ቡድን እና ከሲቪል ማህበረሰብ ጋር በመገናኘት በኮፕ-28 ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
"ኮፕ-28 ከወዲሁ ከፍተኛ ፈተናዎች ገጥመውታል... አሁን የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ የዓለም ሙቀትን በ1.5 ዲግሬ ሴልሺዮስ እንዲገደብ ለማድረግ ከመስማማት ውጪ ሌላ መንገድ የለም" ሲሉም ነው የተናገሩት ቃል አቀባዩ።
ኮፕ-28 የፓሪሱ ስምምነት አፈጻጸም ከመገምገም ባለፈ የአየር ንብረት ፋይናንስ እና የፋይናንሺያል አርክቴክቸር ማሻሻያ የተመለከቱ ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት የሚመከሩበት ይሆናልም የተባለው፡፡
ቃል አቀባዩ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ጀርመን በዘላቂ ኢነርጂ መስክ እያደረጉት ስላለው ትብብር ጸጠይቀው ምላሽ ሲሰጡም “አዎ ብዙ የትብብር ዘርፎች አሉ፡ ከ2017 ጀምሮ በጀርመን እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መካከል በኢነርጂ መስክ ትብብር ሲደረግ ቆይቷል” ብለዋል፡፡
ትብብሩ በ2022 ወደ የታዳሽ ሃይል እና የሃይድሮጅን ስርአቶችን ማቀናጀትን ከፍ ማለቱም ተናግረዋል፡፡