የኮፕ28 ጉባኤ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሱልጣን አል ጃበር ከጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ጋር ተወያዩ
አል ጃበር በቶኪዮ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጋር ተወያይተዋል
የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከአንድ ወር በኋላ በዱባይ ይካሄዳል
የኮፕ28 ጉባኤ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሱልጣን አል ጃበር ከጃፓን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
አመታዊው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት የፊታችን ህዳር ይካሄዳል።
በዱባይ በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የዓለም ሀገራት መሪዎች፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የተቋማት መሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።
የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዝዳንት እና የአረብ ኢምሬት የኢንዱስትሪ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሚንስትሩ ዶክተር ሱልጣል አል ጃበር ጃፓንን ጎብኝተዋል።
ዶክተር ሱልጣን አል ጃበር ከጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጋር በአየር ንብረት ለውጥ፣ በታዳሽ ሃይል ልማት እና በሌሎች ጉዳዮች ተወያይተዋል።
ከኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በተጨማሪ በሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያም መወያየታቸው ተገልጿል።
ሀገራቱ ትብብራቸውን ወደ ቁልፍ ወዳጅነት ለመቀየር የተስማሙ ሲሆን የጋራ ፍላጎቶቻቸውን ሊያሳኩ በሚችሉባቸው ተጨማሪ አጀንዳዎች ዙሪያም ተወያይተዋል ተብሏል።
እንዲሁም ሁለቱ ሀገራት የዓለም ነዳጅ ገበያን ለማረጋጋት፣ በጃፓን-አረብ ኢምሬት የፈጠራ ትብብር እና በታዳሽ ሀይል ልማት ትብብር ዙሪያም በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ኪሺንዳ ከሁለት ወር በፊት በተባበሩት አረብ ኢምሬት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
አልጃበር በቶኪዮ ቆይታቸው ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዮኮ ካሚካዋ ጋርም ተወያይተዋል።