የአውሮፓ ህብርት ኮሚሽን ከዶ/ር ሱልጣን አልጃበር ጋር በቅርበት እየሰራሁ ነው አለ
የአውሮፓ ህብርት ኮሚሽን ቃል አቀባይ በዓለም ዙሪያ ያሉ ፖሊሲ አውጪዎች ለኮፕ 28 ስኬታማነት ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል
በአረብ ኤምሬትስ የሚካሄደው ኮፕ 28 የፓሪሱን ስምምነት ግቦችን ለማሳካት እርምጃ የሚወደስበት እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል
የአውሮፓ ህብርት ኮሚሽን የኮፕ-28 ፕሬዝዳንትና የአረብ ኢሚሬትስ የኢንዱስትሪ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር ካር በቅርበት እየሰራሁ ነው አለ።
የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ቲም ማክፊ ከአል ዐይን ኒውስ ፈረንሳይኛ ቋንቋ ክፍል በተለይ እንደተናገሩት፤ ኮሚሽኑ ከኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ በቅርበት ይሰራል ብለዋል።
“የፓሪሱ ስምምነት ለተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ ፕሬዝዳንትነት በፓርቲዎች መካከል እንደሚዘዋወር ሁሉም በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ ፓርቲዎች በእጩዎቹ እንደሚስማሙ መደንገጉን ያነሱት ቃል አቀባዩ፤ በዚሁ መሰረት ኮሚሽኑ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
እያንዳንዱ ኮንፈረንስ ፕሬዝዳንት በፓሪስ ስምምነት ውስጥ በተካተቱት ነጥቦች መሰረት ዓለምን ወደ ትክክለኛው መንገድ የመመለስ ኃላፊነት አለባቸው ያሉት ቲም ማክፊ፤ ከእነዚህም ውስጥ በጣም አስፈላጊው የአለም ሙቀት መጨመርን ወደ 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ማውረድ ነው ሲሉም ተናረዋል።
የፓሪሱ ስምምነት በዋናነት የክፍለ ዘመኑን የሙቀት መጠን በ2 ዲግሪ ሴልሺየስ ማውረድ እንዲሁም የዓለም ሙቀት ከ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ እንዳለበትም ያመለክታል ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ቃል አቀባይ ቲም ማክፊ በዓለም ዙሪያ ያሉ ፖሊሲ አውጪዎች ለኮፕ 28 ስኬታማነት ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም ፤ የአየር ንብረት ለውጥ የዓለም ስጋት ነው፤ ይህንን መቆጣጠር የሀገራ ሀገራት ኃፊነት ነው ያሉ ሲሆን፤ ሁሉም ሀገራት እና ሚመለከታው ክፍሎቸች በሙሉ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው ብለዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቤርን (ዶክተር) የ2023 የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዝዳንት አድርጋ መሾሟን አስታውቃለች።
የኤምሬትስ የአየር ንብረት ጉዳዬች ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ያገለገሉት ሱልጣን ቢን አህመድ፥ በህዳር 30 2023 የሚጀመረውን የ2023 አለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ።