ከታዳሽ ኃይል የምናገኘውን ኃይል እስከ 2030 በሶስት እጥፍ ማሳደግ አለብን- የኮፕ28 ጉባዔ ፕሬዝደንት
አል ጀባር ባለፈው በአመት በአረንጓዴ ልማት ላይ ክብረወሰን የሰበረ 1 ትሪሊየን ዶላር ኢንቨት መደረጉን ተናግረዋል
ፕሬዝደንቱ እንዳሉት የሚቀጥለው የአየር ንብረት ጉባዔ፣ የአየር ንብረት ግቦችን በ2030 ለማሳካት የሚያስችል መታጠፊያ መሆን አለበት ሲሉም ተናግረዋል
ከታዳሽ ኃይል የምናገኘውን ኃይል እስከ2030 በሶስት እጥፍ ማሳደግ አለብን- የኮፕ28 ጉባዔ ፕሬዝደንት
በአረብ ኢምሬትስ የሚካሄደው የኮፕ28 ጉባዔ ፕሬዝደንት እስከ 2030 ድረስ ከታዳሽ ኃይል የሚገኘውን ኃይል በሶስት እጥፍ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቱ የጋዝ፣ የኃይል እና የኦይል ኩባንያዎች አየርንብረትን በሚቀንሱ ፕሮጀክቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የኮፕ 28 ጉባዔ ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጀባር በአቡዳቢ አለምአቀፍ ፔትሮሊየም ኤግዛቢሽን እና ስብሰብ (አዲፔክ) 2023 ላይ የኢነርጂ ሽግግር ፈጣን እና በደንብ የታቀደ መሆን አለበት ብለዋል።
ፕሬዝደንቱ የሚቀጥለው የአየር ንብረት ጉባዔ የአየር ንብረት ጎሎችን በ2030 ለማሳካት መታጠፊያ መሆን አለበት ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቱ እንደገለጹት ኮፕ28 ጉባዔ የተቀመጡ ግቦችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ይቀይራል።
የታዳሽ ኃይል አቅምን በ2030 በሶስት እጥፍ ማሳደግ ወደ 11ሺ ጊጋዋት ማድረስ እንደሚገባ የገለጹት አል ጀባር ይህ ግብ 85 በመቶ በሚሆነው የአለም ኢኮኖሚ እየተደገፈ ነው ብለዋል።
በዓለም ትልቅ በተባለው ኤዲፔክ ላይ የዘረፉ መሪዎች፣ከመላው አለም የፖሊሲ አውጭዎች እና የፈጠራ ሰዎች የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ ጉዳይ መክረዋል።
ይህ ኤግዚቢሽኑ እስከ ሀሙስ ድረስ ይቀጥላል ተብሏል።
የዓለም የሙቀት መጠንን ለመቀነስ ዓለም በ2030 የአየር ብክለትን 43 በመቶ መቀነስ እንዳለባት አል ጀባር አስገንዝበዋል።
አል ጀባር እንዳሉት ከ20 በላይ የሚሆነ አለም አቀፍ የኦይል እና የጋዝ ኩባንያዎች ብክለትን በ2050 ወይም ቀደም ብሎ ብከሰለትን ወደ ዜሮ ለማድረስ የሚያችል እቅድ ለማዘጋጀት ፍቃደኛ ሆነዋል።
ባለፈው በአመት በአረንጓዴ ልማት ላይ ክብረወሰን የሰበረ 1 ትሪሊየን ኢንቨት መደረጉን ተናግረዋል።