የኮፕ28 ፕሬዝደንት በተለያዩ ዘረፎች ካሉ 800 አለምአቀፍ መሪዎች መልእክት ተቀበሉ
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት በተካሄደው የኮፕ28 ወይም የተመድ የአየር ንብረት ስብሰባ ላይ 198 ሀገራት ተሳትፈውበታል
መሪዎቹ በመልእክታቸው የአየር ንብረት ለውጥ ግቦችን ለማሳካት በሚያደርጉት ጥረት ከዶክተር ጃብር ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል
የኮፕ28 ፕሬዝደንት በተለያዩ ዘረፎች ካሉ 800 አለምአቀፍ መሪዎች መልእክት ተቀበሉ
የኮፕ28 ፕሬዝደንት በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላሳዩት አስተዋጽኦ 800 ከሚሆኑ አለምአቀፍ መሪዎች የእውቅና መልእክት መቀበላቸውን ተናገሩ።
የአረብ ኢምሬትስ የኢንዱስትሪ እና አድቫንስድ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኮፕ28 ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን ቢን መሀመድ አልጃብር ከቢዝነስ፣ ከፋይናንስ፣ ከፊላንትሮፊይ፣ ከፖለቲካ እና ከአካዳሚ ዘርፍ መሪዎች 800 መልእክቶችን ተቀብለዋል።
መሪዎቹ በመልእክታቸው የአየር ንብረት ለውጥ ግቦችን ለማሳካት በሚያደርጉት ጥረት ከዶክተር ጃብር ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል።
በእነዚህ አለምአቀፍ መሪዎች በፈረሙት መልእክት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ትርጉም ያለው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያስፈልጋል ብለዋል።
"ይህ ታሪካዊ ተልእኮ እንደ አንድ ቡድን ሆኖ መስራትን ይጠይቃል" ብለዋል መሪዎቹ።
ከፈራሚዎቹ ውስጥ 300 አለምአቀፍ ስራ አስፈጻሚዎች፣ 34 የፋይናስ መሪዎች እንዲሁም 20 አለምአቀፍ መሪዎች ይገኙበታል።
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት በተካሄደው የኮፕ28 ወይም የተመድ የአየር ንብረት ስብሰባ ላይ 198 ሀገራት ተሳትፈውበታል።