አረብ ኢምሬት በየቀኑ 250 ሺህ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተስማሚ ምግብ እንደምታቀርብ ገለጸች
ኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከሁለት ቀናት በኋላ በዱባይ መካሄድ ይጀምራል
ሀገሪቱ በጉባኤው ወቅት የአከባቢ ብክለትን የሚያስከትሉ አመጋገብ አይኖርም ብላለች
አረብ ኢምሬት በየቀኑ 250 ሺህ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተስማሚ ምግብ እንደምታቀርብ ገለጸች፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር ይመክራል፡፡
ይህ ጉባኤ በተመድ አባል ሀገራት እየተዟዟረ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከያዝነው ሳምንት ጀምሮ በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት በዱባይ ይካሄዳል፡፡
የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አበይት ክስተቶች ምን ምን ናቸው?
የጉባኤው ፕሬዝዳንትም ለተሳታፊዎች ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተስማሚ የሆነ አመጋገብ ስርዓት እንደሚከተል የሀገሪቱ ዜና ወኪል ዋም ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ የተባበሩት አረብ ኢምሬት ለጉባኤው ተሳታፊዎች በቀን 250 ሺህ ምግብ ታቀርባለች የተባለ ሲሆን ምግብ ቤቶች እና ሆቴሎች ምንም አይነት ፕላስቲክ እና ሌሎች ለአካባቢ ብክለት ምክንያት የሚሆኑ እቃዎችን አይጠቀምም ተብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሙሉ ለሙሉ ከእጸዋት የተሰሩ ምግቦች በብዛት ለተመጋቢዎች ይቀርባሉ የተባለ ሲሆን የአፍሪካ፣ እስያ እና ሌሎችም ሀገራት ብርቅዬ የሆነ ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የሆኑ ምግቦችም እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡
ከሁለት ቀናት በኋላ በሚመጀረው የኮፕ28 ጉባኤ ለከባቢ አየር ጤናማነት፣ የታዳሽ ሀይል ሽግግር ስለሚደረግበት፣ በካይ ጋዝ መቀነስ በሚቻልበት እና ለታዳጊ ሀገራት ድጋፍ ስለሚደርገባቸው ሁኔታዎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ በዱባይ ይመክራሉ፡፡