የኮፕ28 ፕሬዝደንት ጉባኤው ስኬታማ እንዲሆን የተጀመረው መነቃቃት ይቀጥላል አሉ
አል ጀባር ይህን ያሉት ከአንድ ወር በኋላ በሚካሄደው የኮፕ28 ጉባኤ ዙሪያ 70 ሚኒስትሮችን እና 100 ልኡካንን በታደሙበት የማጠቃለያ ስብሰባ ላይ ነው
ዶክተር አል ጀባር ተሳታፊዎች በጉባኤው ላይ መግባባት በመፍጠር ወደ አንድነት እንዲመጡ ትኩረት ይደርጋል ብለዋል
የኮፕ28 ፕሬዝደንት ጉባኤው ስኬታማ እንዲሆን የተጀመረው መነቃቃት ይቀጥላል አሉ
የኮፕ28 ፕሬዝደንት እና የአረብ ኢምሬትስ የኢንዱስትሪ እና የአድቫንስድ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጀባር የኮፕ28 ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን የተጀሩ ሰራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
ዶክተር አል ጀባር ተሳታፊዎች በጉባኤው ላይ መግባባት በመፍጠር ወደ አንድነት እንዲመጡ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በዘላቂ ልማት ያሉ ጅምሮች በሚፋጠኑበት ሁኔታ ትኩረት ይደርጋል ብለዋል።
አል ጀባር ይህን ያሉት ከአንድ ወር በኋላ በሚካሄደው የኮፕ28 ጉባኤ ዙሪያ 70 ሚኒስትሮችን እና 100 ልኡካንን በታደሙበት የማጠቃለያ ስብሰባ ላይ ነው።
ወቅቱ የሚፈልገውን ተግባር የማዘግየት እድል አለመኖሩን የገለጹት አል ጀባር ሚኒስተሮች እና ልኡካን በጉባኤው ላይ ስምምነት እንዲደረስ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር አል ጀባር የተመድ ፍሬም ወርክ ኮንቬንሽን ኦን ክላይሜት ቸንጅ ፈራሚ አካላት እንዲነጋገሩ፣ ወደ መግባባት እንዲመጡ እና የኮፕ28ን ጉባኤ ወደስኬት በሚያደርሱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።