የምግብ እና ውሃ ጉዳይን የኮፕ28 ቀዳሚ አጀንዳ ማድረግ እንደሚፈልግ ፋኦ ገለጸ
ዶክተር አብዱል ሀኪም ዋኢር በአረብ ቀጣና ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የግብርና እና የምግብ ምርት ዘርፍ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል
ዶክተር አል ዋኢር በጋዛ ሰርጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በምግብ አቅሮቦት እና ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል
የምግብ እና ውሃ ጉዳይን የኮፕ28 ቀዳሚ አጀንዳ ማድረግ እንደሚፈልግ የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ገለጸ።
የአለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ለአል ዐይን ኒውስ እንደገለፈው የምግብ እና ውሃ ደህንነት ጉዳይን በአረብ ኢምሬትስ በሚካሄደው የኮፕ28 ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ ማድረግ ይፈልጋል።
በፋኦ የኒር ኢስት እና የሰሜን አፍሪካ ተወካይ ዶክተር አብዱል ሀኪም ዋኢር በአረብ ቀጣና ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የግብርና እኔ የምግብ ምርት ዘርፍ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
ይህ ቀጣናው በዓለም በጣም ውሃ አጠር የሚባል ነው።
ዶክተር አል ዋኢር በጋዛ ሰርጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በምግብ አቅሮቦት እና ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በአረቡ አለም ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ከፍተኛ ፍልሰት በሀብት ላይ ከፍተኛ ጫና በማሳደር ድህነት እና አለመረጋጋት እንደሚያስከትል ዶክተር ዋኢር ገልጸዋል።
ዶክተር ዋኢር እንዳሉት ፋኦ በምግብ እና ውሃ ዋስትና እንዲሁም በኢነርጂ ጉዳይ መመጣጠን እንዲኖር ይጥራል።