ፖፕ ፍራንሲስ በኮፕ28 ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ
ፖፕ ፍራንሲስ በዓለም አቀፍ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ሲሳተፉ ይህ የመጀመሪያቸው ይሆናል ተብሏል
28ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት ከቀናት በኋላ ታስተናግዳለች
ፖፕ ፍራንሲስ በኮፕ28 ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ያዘጋጃል።
ይህ ጉባኤ በየዓመቱ በተለያዩ አህጉራት እየተዟዟረ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ጉባኤ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ይዘጋጃል።
ከቀናት በኋላ በዱባይ በሚዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ የቫቲካን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ፖፕ ፍራንሲስ በተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ሲሳተፉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል።
ጉባኤው ከፈረንጆቹ ህዳር 30 እስከ ታህሳስ 12 ይካሄዳል የተባለ ሲሆን ፖፕ ፍራንሲስን ጨምሮ የዓለም ሀገራት መሪዎች በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
በዱባይ ኤክስፖ አዳራሽ እንደሚካሄድ የተገለጸው ይህ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከ15 ዓመት በፊት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ የጸደው ፓሪስ ስምምነት አፈጻጸም ምን ላይ እንደደረሰ ይገመገማል ተብሏል።
በዚህ ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ የተገለጸው ፖፕ ፍራንሲስ በጉባኤው መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የዓለም ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት እንዲሰጡ ንግግር እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።
ሀገራት በተለይም ለምድር የአየር ንብረት መለዋወጥ ዋነኛ ምክንያት ለሆነው የሀይል አጠቃቀም ትኩረት እንዲሰጡ ያሳስባሉም ተብሏል።