ኮፕ28 - ኤምሬትስ ያስተናገደችው ጉባኤ
ለ13 ቀናት በዱባይ ሲካሄድ የነበረው 28ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተጠናቋል
በጉባኤው ላይ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈው ለምድራችን መጻኢ የሚበጁ ውሳኔዎች ተላልፈዋል
የአረብ ኤምሬትሷ ዱባይ ያስተናገደችው ኮፕ28 ታሪካዊ ስምምነት በመድረስ ተጠናቋል።
ጉባኤው ከታዳሽ ሃይል ልማት እስከ ድንጋይ ከሰል ለውይይት ያላቀረበው ጉዳይ የለም።
በጉባኤው የአየር ንብረት ለውጥ በግብርና፣ ጤና፣ የምግብ ዋስትና እና ሌሎች ዘርፎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት የተመለከቱ ውይይቶች ተደርገዋል።
ከ100 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የነበሩት ኮፕ28 ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ነባር ህዝቦች እና የተለያዩ የእምነት ተቋማት መሪዎች ታድመውበት ለምድራችን መጻኢ በሚበጁ ውሳኔዎች ላይ አሻራቸውን አኑረውበታል።