በሰው ልጅ ምክንያት ከሚለቀቅ አጠቃላይ ካርበን ጋዝ ውስጥ ውቂያኖሶች 23 በመቶን እንደሚመጡ ተገልጿል
ተመድ የዓለም ውቂያኖሶች ደህንነት መባባስ እንዳሳሰበው ገለጸ።
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ 11ኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ ምድራችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስ ጉዳትን መቀነስ የሚያስችሉ ምክክሮች እና ውይይቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡
ከዓለም ውሀማ ሀብቶች መካከል አንዱ የሆነው ውቂያኖሶች ደህንነት አደጋ ውስጥ መውደቁ ተገልጿል።
እንደ ተመድ ሪፖርት ከሆነ ውቂያኖሶች በሰል ልጅ ያልተገባ የሀይል አጠቃቀም ምክንያት እየተጎዳ ነው ተብሏል።
በዚህም ምክንያት ዉቂያኖሶች ምድራችን እንድትሞቅ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው የተባለ ሲሆን ወደ ከባቢ አየር ከሚለቀቀው በካይ ጋዝ ውስጥ 90 በመቶው ከውቂያኖሶች እንደሚለቀቅ በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል።
በተለይም በውቂያኖስ ውስጥ ያለው ካርበን ጋዝ መሬት አሲዳማ እንድትሆን እና ከፍተኛ ሙቀት እንድታስመዘግብ ያደርጋልም ተብሏል።
እንደ ዓለም ባንክ ሪፖርት ከሆነ ደግሞ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው ካርበን ጋዝ የውቂያኖስን የውሀ መጠን በመጨመር በሀገራት ላይ የውሀ መጥለቅለቅ እንደሚያደርስም ተገልጿል።
ውቂያኖሶች ለዓለም ኢኮኖሚ በየዓመቱ 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ዶላር የሚያበረክቱ ሲሆን ይህ አሀዝ በ2030 ወደ 3 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሳልም ተብሏል።