የዘንድሮው ኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አረብ ኢምሬት ታስተናግዳለች
በመጭዎቹ ሰባት ዓመታት በዓለም አየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ብዙ እንዲሰራ ተጠየቀ
6ኛው የዓለም አየር ንብረት ድሮው ኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አረብ ኢምሬት ታስተሪያ ብዙ እንዲሰራ ተጠየቀ።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስተባባሪነት የሚዘጋጀው የመንግስት ለአየር ንብረት ለውጥ መድረክ ተካሂዷል።
የአረብ ኢምሬት ኢንዱስትሪ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዶክተር ሱልጣን አህመድ አል ጃቢር በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል።
በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚመክረው "ኮፕ ጉባኤ" ዘንድሮ ማለትም ኮፕ28 በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት የፊታችን ታህሳስ በአቡዳቢ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
የዚህ ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ሱልጣን አህመድ እንዳሉት ቀጣዮቹ ሰባት ዓመታት የዓለም አየር ንብረት መዛባትን በሚያመጡ ችግሮች ዙሪያ ብዙ የሚሰራበት ጊዜ ይሆናል ብለዋል።
ዓለማችን ከእንግዲህ በዘላቂ እና ታዳሽ ሀይል መመራት አለባት ያሉት ዶክተር ሱልጣን በተለይም ጤናማ እና ጊዜውን የጠበቀ የሀይል ሽግግር እንዲደረጉ መደገፍ አለበትም ብለዋል።
ሀገራት እና ተቋማት ከዚህ በፊት ይጠቀሙት ከነበረው በካይ ሀይል ወደ ታዳሽ ሀይል መጠቀም እንዲያመሩ እገዳ ሳይሆን ድጋፍ እንዲደረግም ዶክተር ሱልጣን አሳስበዋል።
በተለይም ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው የካርበን በካይ ጋዝ ሁኔታ እና የምድር ሙቀት ከ1 ነጥብ 5 ድግሪ ሴልሺየስ እንዳይልፍ በጋራ መሰራት አለበትም ብለዋል።