የኮፕ28 ጉባኤ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የበለጠ እንደሚጠቅም ተገለጸ
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ለታዳጊ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተመድ ገልጿል

28ኛው የአለም አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከቀናት በኋላ በዱባይ ይካሄዳል
የኮፕ28 ጉባኤ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የበለጠ እንደሚጠቅም ተገለጸ።
የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ጉዳት በየጊዜው እየተባባሰ የመጣ ሲሆን ይህን መከላከል አላማው ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከቀናት በኋላ በዱባይ ይካሄዳል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የሚያዘጋጅ ሲሆን ሀገራት ደግሞ በየጊዜው ጉባኤን ያዘጋጃሉ።
የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የተባበሩት አረብ ኢምሬት የምታስተናግድ ሲሆን ጉባኤው ከቀናት በኋላ በዱባይ ይካሄዳል።
የተመድ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዳይሬክተር ሪቻርድ ቦልዊን እንዳሉት ይህ ጉባኤ ይበልጥ ታዳጊ ሀገራትን የሚጠቅሙ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበት ገልጸዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ታዳጊ ሀገራትን የበለጠ ጎድቷል የሚሉት ዳይሬክተሩ ጉዳቱን የበለጠ ለመቀነስ ለታዳጊ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
የበለጸጉ ሀገራት በታዳጊ ሀገራት ላይ ከባቢ አየርን የማይጎዱ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ቢያስፋፉ ችግሩን በዘላቂነት መጠበቅ እንደሚችሉም አክለዋል።
የኮፕ28 ጉባኤ መሪዎችን እና ፖሊሲ አውጪዎችን ባንድ መድረክ የሚያገናኝ ጉባኤ በመሆኑ ለምድራችን ጠቃሚ ውሳኔዎች እንደሚወሰኑበትም ተገልጿል።
ዓለም አቀፍ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ወደ ታዳጊ ሀገራት ሄደው እንዲሰማሩ ተመድ ለሀገራቱ እና ኩባንያዎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅበትም ተገልጿል።