ኮፕ28 የዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን ባንድ ላይ ማሰባሰቡ ተገለጸ
አረብ ኢምሬት ለአየር ንብረት ለውጥ ኢንቨስትመንት ፈንድ መቋቋም ያሳየችውን ሰርቢያ አደነቀች
የተመድ ዓመታዊ አየር ንብረት ለውጥ በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት በዱባይ በመካሄድ ላይ ይገኛል
ኮፕ28 የዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን ባንድ ላይ ማሰባሰቡ ተገለጸ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር ይመክራል፡፡
ይህ ጉባኤ በተመድ አባል ሀገራት እየተዟዟረ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት በዱባይ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ዱባይ የሚገኙት የሰርቢያው ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ቩዚች ለአልዐይን እንዳሉት የኮፕ28 ጉባኤ የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ሁሉ ያገናኘ ነው ብለዋል።
በጉባኤው ላይ የተወሰነው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ማካካሻ ፈንድ የዓለም ሀገራት በጋራ ጉዳትን መቀነስ የሚያስችል ጥረት እንዲደረግ ያግዛል ሲሉም አክለዋል።
የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያሳዩት ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንት ቩሲች።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም በዱባይ የተመለከትነው የዓለም ሀገራት መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን መቀነስ የሚያስችሉ ስራዎችን እንድንሰራ የሚያነሳሳ ነውም ብለዋል።