መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን ለመቀነስ ወሳኝ ሚና አላቸው
ድርጅቶች ከሳይንቲስቶች እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ብክለትን ለመቀነስ ውጤታማ ስትራቴጅዎችን እና ቴክኖሎጂዎችን ለመለየት ይሰራሉ
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርድቶች ፋይናንስ፣ እውቀት እና የህዝብ ድጋፍ በማሰባሰብ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር ለመቀነስ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን ለመቀነስ ምን ሚና አላቸው?
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች(ኤንጂኦ) በአለምአቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር ለመቀነስ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
ቁልፍ የሚባሉት አበርክቷቸው የሚከተሉትን ያካትታል።
አድቮኬሲ እና አዌርነስ/ ግንዛቤ ማስጨበጥ
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በዋናነት የአድቮኬሲ ስራ የሚሰሩ ሲሆን በአካባቢያዊ ግንዛቤ የማዳበር፣ መንግስታት እና ኮርፖሬት ድርጅቶች የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጫና ያሳድራሉ። ዘላቂ ልማት በሚያመጡ ፖሊሲዎችን ይደግፋሉ።
ምርምር እና ማሻሻያ
ብዙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር ለመቀነስ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ጥናትና ምርምር ያደርጋሉ። ድርጅቶች ከሳይንቲስቶች እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ብክለትን ለመቀነስ ውጤታማ ስትራቴጅዎችን እና ቴክኖሎጂዎችን ለመለየት ይሰራሉ።
ከማህበረሰብ ጋር መወያየት እና አቅም ግንባታ
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቀጥታ በመገናኘት የአየር ንብረት ለውጥ ችግር እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ግንዛቤ ያስጨብጧቸዋል። ድርጅቶቹ ማህበረሰብን ያካማከለ ፕሮጀክቶችን ያመቻቻሉ፤ ስልጠናም ይሰጣሉ።
ግምገማ እና ተጠያቂነት
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መንግስት እና የኮርፖሬት ተቋማት የአየር ንብረት ለውጥ ለመቀነስ የገቡትን ቁርጥኝነት ተግባራዊ እያደረጉ ስለመሆናቸው ይከታተላሉ። የአየር ንብረት ለውጥ ግቦችን ለማሳከት የሚደረገው ጥረት ያለበትን ደረጃ ይገመግማሉ።
የሰብአዊ እርዳታ እና የአየር ንብረት ፍትህ
ድርጅቶች የአየር ንብረት ለውጥ በሚያመጣው ያልተመጣጠነ ተጽእኖ ምክንያት ጉዳት የሚደርስባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ይደግፋሉ። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲሰፍንም ይሟገታሉ።
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርድቶች ፋይናንስ፣ እውቀት እና የህዝብ ድጋፍ በማሰባሰብ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር ለመቀነስ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።