ፖለቲካ
የአየር ንብረት ለውጥ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ላይ ጅቡቲ ምን አደረገች?
የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቱ በጣም ወጪ ቆጣቢ ከሆኑ የመቋቋሚያ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ነው
የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቱ በጣም ወጪ ቆጣቢ ከሆኑ የመቋቋሚያ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ነው
ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሙቀት ማዕበል ወይም አውሎ ነፋስ ከመምጣቱ 24 ሰዓታት በፊት የሚሰጥ ማስጠንቀቅ የሚከሰተውን ጉዳት በ30 በመቶ ይቀንሳል።
ቀደም ሲል በተባበሩት መንግስታት የታተመ ሪፖርት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች የአየር ሁኔታ ትንበያዎችን የሚያቀርቡ ዘመናዊ መሳሪያ አድርጎ ይመለከታቸዋል።
ስርዓቱ በጣም ወጪ ቆጣቢ ከሆኑ የመቋቋሚያ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ነው።
በሰዓቱ የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ ሰዎች የጎርፍ አደጋን ለመገመት፣ ቁሶችን ለማከማቸት ወይም በአንዳንድ ከባድ ሁኔታዎች ቤታቸውን በመልቀቅ ቀድመው እርምጃ እንዲወስዱ ያስችላል።
ባለፈው ዓመት ጅቡቲ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የሚያጠና የምርምር ጣቢያ ከፈተች።
በዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ በጋራ የተመሰረተው ጣቢያው በድርቅ እና በረሀብ ለተጋለጠችው ሀገር የውሃ እና የምግብ ሀብቶች አያያዟን ለማሻሻል ረድቷታል።
ተቋሙ የአካባቢ እና የአየር ንብረት ምርምር ዜዴዎችን በመጠቀም በሀገሪቱ የአየር ንብረት መላመድ እና የመቋቋም ላይ የፖሊሲ ውሳኔዎችን እና ለመላው የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና በአበርክቶ ሊሆን ይችላል።