ፖለቲካ
ኮፕ28 ጉባኤ ስኬታማ መሆኑን የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ገለጹ
ፕሬዝዳንት ማክሮን የአየር ንብረት ለውጥ ስራዎች የበለጠ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል ብለዋል
የተመድ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በዱባይ በመካሄድ ላይ ይገኛል
ኮፕ28 ጉባኤ ስኬታማ መሆኑን የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ገለጹ።
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አራተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
በጉባኤው ላይ የተገኙት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከአልዐይን ጋር ባደረጉት ቆይታ ኮፕ28 ስኬታማ ጉባኤ መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ማካካሻ ፈንድ መቋቋሙ የኮፕ28 ትልቁ ስኬት ነውም ብለዋል።
የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ምድራችን ላይ ከሚደርስ ተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ሊታደጉ የሚችሉ ውሳኔዎች እንደተወሰኑም ፕሬዝዳንት ማክሮን ጠቅሰዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ፈንዱ የዓለማችን ሀገራት ከድንጋይ ከሰል እና ሌሎች በካይ የሀይል አማራጮችን በመተው ወደ ታዳሽ ሀይል እንዲያዞሩ ያደርጋልም ብለዋል።
የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አዘጋጇ የተባበቱት አረብ ኢምሬት ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ 30 ቢሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ አስታውቃለች።