79 ሀገራት የፈረሙበት የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳን የሚያግዝ ዲክላሬሽን ይፋ ሆነ
የኮፕ28 ስብሰባ ፕሬዝደንት ጽ/ቤቱ የዲክላሬሽኑን ፈራሚዎች ይፋ አድርጓል
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 የአየር ንብረት ስብሰባ ዛሬ አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል
79 ሀገራት የፈረሙበት የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳን የሚያግዝ ዲክላሬሽን ይፋ ሆነ
በአረብ ኢምሬትሷ ዱባይ እየተካሄደ ባለው የኮፕ28 ስብሰባ የ'አየር ንብረት፣ ሪሊፍ፣ ማገገም እና ሰላም ዲክላሬሽን' ይፋ ተደርጓል።
የኮፕ28 ስብሰባ ፕሬዝደንት ጽ/ቤቱ የዲክላሬሽኑን ፈራሚዎች ይፋ አድርጓል።
ዲክላሬሽኑ ግጭት እና የአየር ንብረት ለውጥ ለሚያመጡት ችግር በከፍተኛ መጠን ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦችን ለመርዳት የሚደረገውን አለምአቀፍ ጥረት ለማፋጠን ያግዛል ተብሏል።
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የሚያስችል እርምጃ ለመውሰድ እና ኢንቨስትመንት ለመጨመር ቁርጠኝነታቸውን ያሳዩ 70 መንግስታት እና 39 ተቋማት ዲክላሬሽኑን ፈርመዋል።
የአረብ ኢምሬትስ የኮፕ28 ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ተወካይ እና ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር መጅድ አል ሱዋዲ የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ሁሉንም ህዝብ የሚያጠቃ በመሆኑ የዲክላሬሽኑ መፈረም አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በዛሬው እለት ከዲክላሬሽኑ በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን አደጋ ለመቀነስ የሚያስችል 'ዲሳስተር ማኔጅመንት ቻርተር' የተባለ የትብብር ማዕቀፍም ይፋ ሆኗል።
ዲክላሬሽኑ እና ቻርተሩ አለምአቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችሉ በኮፕ28 የተነደፉ ኢኒሼቲቮች ናቸው።
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 የአየር ንብረት ስብሰባ ዛሬ አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
በዚህ ስብሰባ የ198 ሀገራት ተወካዮች እና በርካታ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እየተሳተፉ ይገኛሉ።