ምድራችንን ከከፋ የአየር ንብረት ለውጥ የሚታደጉ ተጨማሪ ጥረቶች እንደሚካሄዱ ተገልጿል
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አራተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር ይመክራል፡፡
ይህ ጉባኤ በተመድ አባል ሀገራት እየተዟዟረ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት በዱባይ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
አራተኛ ቀኑን የያዘው ይህ ጉባኤ በዛሬው ውሎው የአየር ንብረት በሰው ልጆች ጤና ላይ እያደረሰው ባለው ጉዳት ዙሪያ ትኩረቱን ይደርጋል ተብሏል፡፡
በዛሬው ውሎም የጤና ባለሙዎች፣ ሲቪል ድርጅቶች፣ የቢዝነስ መሪዎች፣ እና ሌሎችም ጉዳጠዩ የሚመለከታቸው አካላት ይሳተፋሉ የተባለ ሲሆን ለሰው ልጆች ጤና ተስማሚ የሚሆኑ የውሳኔ እና ሙያዊ አስተያየቶች እንደሚነሱበት ይጠበቃል፡፡
የጤና ሚኒስትሮች እና ከዚህ ጋር የተያያዙ ተመራማሪዎች ከገንዘብ ባለሙያዎች እና ተቋማት መሪዎች ጋር የሚደረገው ይህ ውይይት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ስለሚመጡ በሽታዎች መከላከል የሚቻልባቸው ጉዳዮች የዛሬው ዋና አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ካሳለፍነው ሀሙስ ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን የጉባኤው አዘጋጅ የሆነችው አረብ ኢምሬት ተጨማሪ ድጋፎችን እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡
ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጮችን መደገፍ እንደሚገባ የአውሮፓ ህብረት ገለጸ
ሀገሪቱ ላልተረጋጉ ሀገራት የውሃ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ 150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከግል ባለሀብቶች እና የንግድ ኩባንያዎች 18 ቢሊዮን ድርሃም ወይም 5 ቢሊዮን ዶላር በመሰብሰብ ለአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ድጋፍ እንደምታውልም ገልጻለች፡፡
በዱባይ እየተካሄደ ባለው 28ኛው የተመድ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የ200 ሀገራት መሪዎች፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎች፣ የተቋማት መሪዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
አረብ ኢምሬትን ጨምሮ የተለያጠዩ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ፈንድ ያዋጡት ገንዘብ 400 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል፡፡