የኮሮና ቫይረስ በሌሎች በሽታዎች ህክምና አሰጣጥ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል ተባለ
የኮሮና ቫይረስ በታዳጊ ሀገራት ለህጻናት የሚሰጠውን ህክምና አስቸጋሪ አድርጎታል-የአለም ጤና ድርጅት
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመደበኛ የጤና አገልግሎት ላይ ጫና ማሳደሩን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመደበኛ የጤና አገልግሎት ላይ ጫና ማሳደሩን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በመደበኛ የጤና አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) የኮሮና ቫይረስ በታዳጊ ሀገራት ለህጻናት የሚሰጠውን ህክምና አስቸጋሪ እንዳደረገው ትናንት በቪዲዮ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ፣ምስራቅ አውሮፓ፣ደቡብ አሜሪካ እና በአንዳንድ የእስያ ሃገራት የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ እንዳሳሰበው አስታውቋል፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ በቀጣይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ብዙ የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ገልጸው ስርጭቱን ለመግታት ድርጅቱ የሚችለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት፡፡
አሁን ላይ የኮሮና ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱ በህጻናት ህክምና አሰጣጥ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ብለዋል፡፡ አሁን ላይ በየፊናው ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ለኮሮና ወረርሽኝ ክትባት በመሆኑ በተለያዩ በሽታዎች የታመሙ ህጻናትን ለማከም አስቸጋሪ ሆኗል ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ህጻናት በኮሮና ቫይረስ የመጠቃት ዕድላቸው አነስተኛ ቢሆንም በሌሎች በሽታዎች ሊያዙ ስለሚችሉ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት፡፡
አሁን ላይ 13 ሚሊዮን ሰዎች መደበኛ ህክምና ባለማግኘታቸው በፖሊዮ፣በኮሌራ፣በቢጫ ወባና ማጅራት ገትር በሽታዎች እየተሰቃዩ መሆኑንም ነው የዓለም ጤና ድርጅት ያስታወቀው፡፡ የተለያዩ በሽታዎችን ክትባት ለመስጠት መቸገራቸውን 21 ሃገራት ሪፖርት ማድረጋቸውንም ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገልጸዋል፡፡
ይህ ተፈጠረውም ሃገራት ድንበሮቻቸውን፣ የአየር ክልላቸውን በመዝጋታቸውም እንደሆነ ጋቪ ግሎባል ቫክሲን የተባለውን ተቋም ጠቅሰው ጸናግሯል፡፡ ከሰሃራ በታችም የወባ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የገለጹት ዋና ዋና ዳይሬክተሩ ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምን ያህል በሌሎች በሽታዎች ህክምና ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ አብራርተዋል፡፡
በመሆኑም ይህ ችግር ከዚህ እንዳይብስ የሌሎች በሽታዎችን ህክምና መቀጠል ያስፈልጋል ዶ/ር ቴድሮስ የህጻናትን ህክምናም ትኩረት መስጠት ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ብለዋል፡፡