በመላው ዓለም እስካሁን የሟቾች ቁጥር ከ66,500 በላይ ሲደርስ የተጠቂዎች ደግሞ ከ 1.2 ሚሊዮን በላይ ነው
በመላው ዓለም እስካሁን የሟቾች ቁጥር ከ66,500 በላይ ሲደርስ የተጠቂዎች ደግሞ ከ 1.2 ሚሊዮን በላይ ነው
ዩኤስ አሜሪካ በአንድ ቀን 1,344 ሰዎች የሞቱባት ሲሆን ይሄም ቫይረሱ ከተከሰተ ወዲህ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛው የሞት ቁጥር ነው፡፡
በሀገሪቱ እስካሁን የሞቱ ሰዎች ቁጥር 8,500 ገደማ ደርሷል፡፡ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ312,000 በልጧል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቫይረሱን ለመከላከል በምናደርገው ጥረት ቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት እጅግ ወሳኝ ናቸው ብለዋል፡፡ በነዚህ ሳምንታት የበርካታ ታማሚዎች ህይወት ሊያልፍ እንደሚችልም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡
በአሜሪካዋ ኒው ዮርክ ግዛት ወደ 20 በመቶ ፖሊሶች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል
በአሜሪካ በኮሮና በከፍተኛ ደረጃ በተጠቃችው ኒው ዮርክ 18.5 በመቶ የሚሆኑ መለዮ ለባሽ ፖሊሶች በቫይረሱ መያዛቸውን የኒው ዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት አስታውቋል፡፡ በግዛቲቱ 1,775 መለዮ ለባሽ ፖሊሶች እና 260 ሲቪል የዲፓርትመንቱ አባላት እስከ ትናንት ድረስ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡
ባጠቃላይ በልእለ ሀያሏ ሀገር አሜሪካ ከሚገኙ ከ312,000 በላይ የኮሮና ታማሚዎች ከ 113,000 በላይ የሚሆኑት የኒው ዮርክ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ ኒው ዮርክ ብቻዋን የጣሊያንን ያክል ታማሚዎች ይገኙባታል፡፡
ስፔን አሜሪካን በመከተል በተጠቂዎች ቁጥር ሁለተኛ ሆናለች
ስፔን ደግሞ በትናንትናው እለት ብቻ 809 ሞት አስተናግዳለች፡፡ ስፔን የተጠቂዎቿ ቁጥር ከ126,000 በላይ የደረሰ ሲሆን ከ124,000 በላይ ተጠቂዎች ካሏት ከጣሊያን በልጣለች፡፡ በስፔን እስካሁን 34,219 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡ ምንም እንኳን በየእለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመር ላይ ቢሆንም መጠኑ ግን ከወትሮው በማነስ ላይ ይገኛል ነው የተባለው፡፡
በኢኳዶር አስከሬኖች ቀባሪ እያጡ ነው
እስካሁን 3465 የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች የተገኙባት ኢኳዶር ሰው በሚበዛበት የወደብ ከተማዋ ጓያቁል የማህበራዊ አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ የሞቱ ሰዎች ቀባሪ በማጣት ላይ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡ ከሟቾቹ መካከል ምን ያክሉ በኮሮናቫይረስ እንደሞቱ በግልጽ ባይታወቅም የሟች ቤተሰቦች ግን ረዳት በማጣታቸው አስከሬኖችን በረንዳ ላይ አውጥተው በማስቀመጥ ላይ ናቸው፡፡ በከተማዋ የሚገኙ ሆስፒታሎች በታማሚዎች መሙላታቸውን እና ተጨማሪ በሽተኞችን ለማስተናገድ የሚሆን አልጋ እንደሌላቸው የሲኤንኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡
በህንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 3,374 ደረሰ
የህንድ ጤና ኒስቴር እንዳስታወቀው እስከ ዛሬ እሁድ ጠዋት በሀገሪቱ 3,374 የቫይረሱ ተጠቂዎች ተለይተዋል፡፡ ከነዚህም 302 ታማሚዎች ትናንት የተለዩ ናቸው፡፡ ባጠቃላይ እስካሁን በሀገሪቱ 77 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡ በህንድ ከመጋቢት 15 ጀምሮ የ21 ቀናት የእንቅስቃሴ እገዳ ታውጆ መላው የሀገሪቱ ዜጎች በቤታቸው መሆናቸው ይታወቃል፡፡
በመላው ዓለም እስካሁን የሟቾች ቁጥር ከ66,500 በላይ ሲደርስ የተጠቂዎች ደግሞ ከ 1.2 ሚሊዮን በላይ ነው፡፡
ምንጭ፡- ሲኤንኤን