ኮሮናቫይረስ 'በሞባይል ስልኮች እና በጥሬ ገንዘብ ለአራት ሳምንታት መቆየት ይችላል' ተባለ
ጥናቱ የበሽታውን ስርጭት በትክክል ለመተንበይ እና ለመግታት ይረዳል ብለዋል ተመራማሪዎቹ
ቀዝቃዛ የአየር ጸባይ ለቫይረሱ ረዥም እድሜ እንደሚሰጠው የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች ገልጸዋል
ኮሮናቫይረስ 'በሞባይል ስልኮች እና በጥሬ ገንዘብ ለአራት ሳምንታት መቆየት ይችላል' ተባለ
በአውስትራሊያ ከፍተኛ የስነ-ሕይወት ደህንነት ላቦራቶሪ የተደረገው ጥናት ኮሮናቫይረስ በገንዘብ ኖቶች ፣ በመስታወት እና በሌሎች የተለመዱ ቦታዎች ላይ ለሳምንታት ተላላፊ ሆኖ ሊቆይ ይችላል፡፡
በአውስትራሊያ የበሽታ ዝግጁነት ማዕከል ሳይንቲስቶች ቫይረሱ “እጅግ በጣም ጠንካራ” እንደሆነ እና የሞባይል ስልክ ማያ ገጾች (ስክሪኖች) ፣ ፕላስቲኮች እና የገንዘብ ኖቶችን በመሳሰሉ ወጥ በሆኑ ስፍራዎች ላይ ለ 28 ቀናት ፣ በመደበኛ የ20 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ፣ በሕይወት መቆየት እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
ለ 17 ቀናት ከሚቆየው የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ጋር ሲነጻተር የኮሮናቫይረስ እድሜ ከፍተኛ የሚባል ነው፡፡
በአንዳንድ ቦታዎች ላይ በ40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የቫይረስ ዕድሜ ከአንድ ቀን በታች እንደሆነ ዛሬ በቫይሮሎጂ ጆርናል ላይ ይወጣል የተባለው ጥናት ያመለክታል፡፡
የጥናቱ ግኝት ቫይረሱ በቀዝቃዛ የአየር ጸባይ ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ በሕይወት እንደሚቆይና ይህም ቫይረሱን በክረምት ወቅት መቆጣጠርን ይበልጥ አስቸጋሪ እንደሚያደርገው አረጋግጧል፡፡
እንደ ጥጥ ያሉ ውስብስብ እና ወጥ ካልሆኑ ነገሮች ጋር ሲነጻጸር ኮሮናቫይረስ ቀዳዳ በሌለው እና ወጥ በሆነ ቦታ ላይ ረዘም ላለ ጊዜ የመኖር አዝማሚያ አለው ነው የተባለው፡፡
የተገኘው ውጤት “በመደበኛነት እጅን መታጠብ እና ንጣፎች ማጽዳትን የመሳሰ ጥሩ ልምምዶችን አስፈላጊነት” ያጠናክራል ብለዋል የማዕከሉ ምክትል ዳይሬክተር ዴቢ ኤግልስ፡፡
ዘ ናሺናል እንደዘገበው ጥናቱ የበሽታውን ስርጭት በትክክል ለመተንበይ እና ለመግታት ይረዳል ብለዋል ተመራማሪዎቹ፡፡